የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተቀናቃኛቸውን ጆ ባይደንን፣ ከፍተኛ ፉክክር ባለባቸው አምስት ወሳኝ ግዛቶች እየመሩ እንደኾነ፣ ዐዲስ የወጣ ፖለቲካዊ የሕዝብ አስተያየት አመልክቷል።
የባይደን የዕድሜ መግፋት እና የኢኮኖሚው ጉዳይ፣ እንዲሁም በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ጦርነት መፈንዳቱ፣ ድምፅ ሰጪዎቹን የሚያሳስቡ ጉዳዮች እንደኾኑ፣ ፖለቲካ መር የሕዝብ አስተያየቱ ጠቁሟል።
የቪኦኤዋ አኒታ ፓወል ከዋይት ሐውስ የላከችው ዘገባ ነው፡፡
መድረክ / ፎረም