በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮቪድ-19 ክትባት ተራደሽነት


 ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ
ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ

የዩናይትድ ስቴትስ የኮቪድ-19 ክትባት ድሆች ሃገሮች ለማዳረስ የሚንቀሳቀሰውን ዓለም አቀፍ ህብረት እንደምትቀላቀል ዋናው የሃገሪቱ የተላላፊ በሽታዎች አዋቂ ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ አስታወቁ።
የዩናይትድ ስቴትስ የአለርጂ እና የተላላፊ በስታዎች ተቋም ዋና ዳይሬክተርና የአዲሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጤና ጉዳዮች ዋና አማካሪ ፋውቺ ዛሬ ሃሙስ ከዓለም የጤና ድርጅት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ጋር በርቀት በቪዶዮ በተካሄደ ስብሰባ ባደረጉት ንግግር “ኮቬክስ” በሚል ምህጻረ ቃል በዓለሙ የጤና ድርጅት መሪነት የተቋቋመውን የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽነት ተቋም ሃገራቸው እንደምትቀላቀል ገልጸዋል።
በተጨማሪም ሃገራቸው ለዓለም የጤና ድርጅት የሚገባትን መዋጮ ትከፍላለች ብለዋል።
አዲሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ትናንት ቃለ መሃላቸውን ከፈጸሙ በኋላ ስራቸውን እንደጀመሩ ባወጡት የአስፈጻሚ ትዕዛዝ ሃገራቸው ከዓለሙ የጤና ድርጅት ጋር ግንኙነቷን እንድትቀጥል መመሪያ አስተላልፈዋል።
ባለፈው ግንቦት ወር ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የዓለሙን የጤና ድርጅት ቻይና በሃገርዋ ዉሃን ከተማ ስለተቀሰቀሰው ኮሮናቫይረስ ጉዳይ ዕውነቱን እንድትደብቅ ረድቷል ብለው በመወንጀል ዩናይትድ ስቴትስን ከድርጅቱ ለማስወጣት መወሰናቸው የሚታወስ ነው።
የዓለም የጤና ድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዶ/ር አንተኒ ፋውቺን መግለጫ ተከትሎ በሰጡት ቃል "ዛሬ ለዓለም አቀፍ ጤና ጥሩ ቀን ሆነ” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG