በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለሳህል አካባቢ ሀገሮች 60ሚሊዮን ዶላር ልትለግስ ነው


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ የሳህል አካባቢ ሀገሮች ለሚያካሂዱዋቸው ፀረ ሽብርተኛ ጥረቶች መርጃ 60ሚሊዮን ዶላር ልትለግስ ቃል ገባች።

ዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ የሳህል አካባቢ ሀገሮች ለሚያካሂዱዋቸው ፀረ ሽብርተኛ ጥረቶች መርጃ 60ሚሊዮን ዶላር ልትለግስ ቃል ገባች።

ዛሬ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ይፋ ያደረጉት ርዳታው ቡርኪና ፋሶ፣ቻድ፣ ማሊ፣ ሞሪታኒያ እና ኒጀር በዚሁ የአውሮፓውያን ዓመት ውስጥ ለመሰረቱት የጋራ ግብረ ኃይል ድጋፍ ለመስጠት ይውላል።

ሽብርተኝነትን ድል ለመምታት አሸባሪ ቡድኖች በማናቸውም አህጉር ውስጥ መሸሸጊያ እንዳያገኙ መድረግን ይጠይቃል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲለርሰን አስገንዝበዋል።

የሚሰጠው የገንዘብ ዕርዳታ “የእስልምና መንግሥት” ብሎ ራሱን በሚጠራው ቡድንና በግብረ አበሮቹ እንዲሁም በሌሎች ሽብርተኛ ቡድኖች አደጋ የተደቀነባቸው የክልሉ አጋሮቻችን ፀጥታቸውን ለማረጋገጥ የሚያካሂዱትን ትግል ያጠናክርላቸዋል ብለዋል።

በቅርቡ ከእስልምና መንግሥት ቡድን ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች ደቡብ ምዕራብ ኒጀር ውስጥ በዩናይትድ ስቴትስና በኒጀር ወታደሮች ላይ ባደረሱት ጥቃት አራት አሜሪካውያን ወታደሮች መግደላቸው ይታወሳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG