በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ራሽያ ስለ አሜሪካው የጋዝ ማስተላለፊያ ጥቃት አስተባበለች


በጋዝ ማስተላለፊያው ላይ በደረሰው ጥቃት የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ ነው
በጋዝ ማስተላለፊያው ላይ በደረሰው ጥቃት የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ ነው

ራሽያ ከፊል የዩናይትድ ስቴትስ ምስራቃዊ ግዛትን የሚሸፍነውን የኮሎንያል የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመርን፣ በማሽመደመድ ፈጽማዋለች የተባለውን የሳይበር ጥቃት ክስ አስተባብላለች፡፡ የባይደን አስተዳደር የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ለመለካለከል እምርጃዎችን እየወሰደ ሲሆን፣ አሸከርካሪዎችም በነዳጅ ዋጋ ላይ የተደረገውን ጭማሪ መመልከት ጀምረዋል፡፡

ባለሥልጣናቱ ይህን ችግር ተከትሎ የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ለማረጋጋት በሚሞክሩበት በዚህ ወቅት፣ አንዳንድ አሜሪካውያንም በየነዳጅ ማደያው ተጨማሪ ዋጋ መክፈል ጀምረዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዷ የሆኑትፓትርሺያ ባምጋርደነር እንዲህ ይላሉ

“ወደ አንድ ሌላ ተጨማሪ ጭንቀት ውስጥ የሚከተን አንድ ትልቅ ነገር ነው፡፡”

ኮለንያል የጋዝ ማስተላለፊያ መስመር፣ ከፊሉን ምስራቃዊ የአሜሪካ ግዛት፣ የነዳጅ አቅርቦት የሚያዳርስ ሲሆን፣ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በደረሰበት ጥቃት ስራ አቁሟል፡፡

ጥቃቱ የጋዝ ማስተላለፊያውን መስመር የኮምፒውተር ስርዓት ጠልፎ ቆላልፎ በማገት፣ የገንዘብ ክፍያ መጠየቅ ወይም ransomware attack የተባለው ጥቃት፣ የተፈጸመበት መሆኑም ተመልከቷል፡፡

እንዲህ ዓይነቶቹ ጥቃቶች ትላልቅ የንግድ ኩባንያዎችንም ሆነ የመንግሥት ተቋማትን፣ የኢንተርኔት መረቦች ጠልፎ በማገት፣ ወይም አገልግሎታቸውን በማሽመድመድ፣ የገንዘብ ክፍያ መጠየቅ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ራሽያ ስለ አሜሪካው የጋዝ ማስተላለፊያ ጥቃት አስተባበለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:04 0:00

ኤፍ ቢ አይ፣ እንደዚህ ዓይነቶቹን ወንጀል የሚሰሩት መሰረታቸውን በራሽያ ወይም በምስራቅ አውሮፓ ያደረጉና “ዳርክ ሳይድ” ተብለው የሚጠሩ ቡድኖች መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

የዋይት ሀውስ የፕሬስ ሴክረተሪ፣ ጄን ሳኪም ደግሞ እንዲህ ብለዋል

“ለማንኛውም ስለጉዳዩ አንድ ውሳኔ ላይ ከመድረሳችን በፊት፣ የመረጃ ተቋሞቻችን መምረመው የሚደርሱበትን ድምዳሜ እንጠባበቅ፡፡”

ዳርክ ሳይድ የተባለው ቡድን “እኛ የምንፈልገው ገንዘብ ብቻ ነው፡፡ ሌላ ስለ መልካምድራዊው ፖለቲካ ጉዳያችን አይደለም” ማለቱም ተመልክቷል፡፡

ትንናት ማክሰኞ፣ ስለጉዳዩ አስተያየታቸውን የሰጡት፣ የራሽያ መንግሥት ቃል አቀባይ፣ ዲምትሪ ፔስኮቭ፣ አገራቸው እጇ እንደሌለበት በመግለጽ

“ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚደርሰብንን ክስ ሁሉ አጥብቀን እንቃወማለን፡፡” ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

ባለፈው ሚያዝያ፣ ሶላር ዊንድ በተባለው ትልቁ የቴክኖሎጂ ድርጅት ላይ፣ አድርሳለች በተባለችው ተመሳሳይ የሳይበር ጥቃት፣ የባይደን አስተዳደር፣ ራሺያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ መጣሉ ይታወቃል፡፡

የሳይበር ጥቃት ባለሙያዎች ደግሞ፣ ራሽያን ጨምሮ በዓለም ላይ እንዲህ ዓይነቶቹን ጥቃቶች ለማስቆም የሚያስችል፣ ዓለም አቀፍ ስምምነትና ድንጋጌ መኖር አለበት ይላሉ፡፡

በዊልሰን ማዕከል፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ፕሮግራም ድሬክተር የሆኑት ሜግ ኪንግ እንዲህ ብለዋል

“ይህን ጥቃት ሊያስቆም የሚያስችል አስራር ወይም ዘዴ ካልፈጠርን ድረስ ፣ በራሽያና በአካባቢዋ ባሉ አገሮች ውስጥ ያሉ ወንጀለኞች የንግድ ኩባንያዎችን የስራ መዋቅርና መረጃዎች እያገቱ ገንዘብ የሚጠይቁበን መንገድ ከባድ እስካላደረግ ነው ድረስ፣ የንግድ ድርጅቶች መረጃዎቻቸውን ቅጂ ለመጠባበቂያነት እንዲያስቀምጡ እስካልረዳናቸው ድረስ በመሠረተ ልማቶች ሥራ ላይ የተሰማሩ ሁሉ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ እስከ ምን ድረስ ሊሄድ እንደሚችል እንዲያዩ እስካላደረግን ድረስ ይህ ነገር ይቀጥላል፡፡”

ጥቃቱ የተፈጸመበት የኮሎንያል የጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ባለቤት፣ አገልግሎቱን መልሶ ለመጀመር እየሠራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የባይደን አስተዳደርም ይህን ተከትሎ የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ለማሟላት እርምጃዎችን እየወሰደ ነው፡፡

ከእነዚህ ውስጥ አነስተኛ ጥራት ያላቸውን የጋዝ ዓይነቶች ቀላቀሎ አገግሎት ላይ ለማዋል፣ እንዲሁም የባቡር መስመሮች ነዳጅ ወደ ተቋረጠባቸውና፣ ጥረቱ በጣም ወደ ተከሰተባቸው አካቢዎች እንዲያጓጉዙ በማድረግ እየሠራ መሆኑን አመልክቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴት የኃይል ሚኒስትር ጀኒፈር ግራንሆልም እንዲህ ይላሉ

“የጋዝ እጥረት ስላለን አይደለም ይህ ነገር የተከሰተው፡፡ የአቅርቦት መስመራችን ስለተሰናከለ ነው፡፡ ስለዚህ ነገሮች በቅርቡ ወደነበሩበት ይመለሳሉ፡፡”

አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፣ አስተዳደሩ በዩናይትድ ስቴትስ ወደቦች መካከል ያለው የነዳጅ ማጓጓዝ አገልግሎት፣ አሜሪካ ስሪትና፣ ንብረትነታቸው የአሜሪካውያን በሆኑ ድርጅቶችና መርከቦች ብቻ እንዲከናወን የሚያዘውን የፌደራል መንግሥቱን ህግ፣ የሚያላላበት ሁኔታም ካለ እየተዘጋጀ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የቪኦኤ የዋይት ሀውስ ዘጋቢ ፓትሲ ውዳክስዋራ ከላከቸው ዘገባ የተወሰደ፡፡

XS
SM
MD
LG