በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፊላዴልፊያ የተለያዩ ግዛቶችን የሚያገናኘው አውራ ጎዳና-95 ላይ የሚገኘው ድልድይ ተደረመሰ


በዩናይትድ ስቴትስ ፊላዴልፊያ ክፍለ ግዛት፣ የተለያዩ ግዛቶችን የሚያገናኘው አውራ ጎዳና - 95
በዩናይትድ ስቴትስ ፊላዴልፊያ ክፍለ ግዛት፣ የተለያዩ ግዛቶችን የሚያገናኘው አውራ ጎዳና - 95

በዩናይትድ ስቴትስ ፊላዴልፊያ ክፍለ ግዛት፣ የተለያዩ ግዛቶችን የሚያገናኘው አውራ ጎዳና - 95 ተብሎ በሚታወቀው መንገድ ላይ፣ ከፍ ብሎ የተሠራ አንድ ድልድይ፣ ትላንት እሑድ ተደርምሷል፡፡

በዚኽ የተነሣም፣ የአገሪቱን ሰሜን፣ ደቡብ እና በምሥራቅም እስከ ባሕር ዳርቻ የሚያደርሰውን መንገድ በመዝጋት፣ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር በሚገኘበት በሰሜን ምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትስ፣ የትራፊክ መስተጓጎል ሊፈጥር እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

ድልድዩ የተሰበረው፣ ትላንት እሑድ፣ ተቀጣጣይ ነገሮችን ጭኖ የነበረው የጭነት ተሽከርካሪ፣ በእሳት በመቀጣጠሉ እንደኾነ፣ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

በሰሜናዊ ምሥራቅ የከተማዪቱ ክፍል፣ ከላይ ከነበረው አውራ ጎዳና፣ አንድ ግዙፍ የኮንክትሪት ንጣፍ፣ ከታችኛው መንገድ ላይ ሲወድቅ ታይቷል፡፡

ክሥተቱን፣ በስልካቸው ካሜራ ቀርጸው ያስቀሩት፣ ጡረተኛው የፖሊስ ኀምሳ አለቃ፣ ወደ ፊላዴልፊያ አውሮፕላን ማረፊያ ሲነዱ፣ ከአውራ ጎዳናው፣ ጥቁር ጢስ ወደ ላይ ሲወጣ ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ማርክ ፉሴቲ የተባሉ ነዋሪም፣ እሳቱን አልፈው እንደነዱ፣ መንገዱ ቁልቁል እየወረደ፣ ድልድዩ ከመደርመሱ በፊት፣ ሰዎች መኪናዎቻቸውን በያሉበት ሲያቆሙ፣ በኋላ መመልከቻ መስተዋታቸው ማየታቸውን ገልጸዋል፡፡

የፔንስልቬኒያው አገረ ገዥ ጆሽ ሻፒሮ፣ ይህን አውራ ጎዳና - 95 መልሶ ለመጠገን፣ ብዙ ወራት ሊወስድ ይችላል፤ ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG