አሜሪካ ለ90 ቀናት የውጪ ርዳታ እንደሚቋረጥ ብታስታወቅም፣ ‘የፕሬዝደንቱ የኤድስ አስቸኳይ ጊዜ ርዳታ’ ወይም ‘ፔፕፋር’ በሚባል የሚታወቀው ፕሮግራም እንደማይቋረጥ ታውቋል።
ፔፕፋር በዓለም መሪ የሆነ በኤድስ ላይ የሚሠራ ፕሮግራም ሲሆን፣ ሕይወት አድን ፕሮግራሞች እንዲቀጥሉ በመወሰኑ የ90 ቀናት እገዳው እንደማይመለከተው ታውቋል።
ፕሬዝደንት ትረምፕ ሥልጣኑን ደግመው በተረከቡ በሰዓታት ውስጥ ነበር “አሜሪካ ትቅደም” ከሚለው የውጪ ፖሊሲያቸው ጋራ የሚጣጣሙ መሆናቸው እስከሚጣራ ለውጪ ሃገራት የሚሰጡ ዕርዳታዎች ለ90 ቀናት እንዲቆሙ ያዘዙት፡፡
የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ እንደሚቀጥል ቀደም ብለው አስታውቀው የነበረ ሲሆን፣ ቆየት ብለው ደግሞ ደግሞ ሕይወት አድን መድሃኒቶችና የሕክምና አገልግሎቶች እንዲሁም የምግብና የመጠለያ ዕርዳታዎች እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
በዓለም በኤች አይ ቪ ከተያዙት ከሁለት ሶስተኛ በላይ ወይም ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የቫይረሱ ተጠቂዎች በፔፕፋር ፕሮግራም በቀጥታ የሚረዱ መሆኑም ታውቋል።
መድረክ / ፎረም