በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮቿ የሐማስን የገንዘብ ምንጭ ለማድረቅ ግብረ ኃይል አቋቋሙ


ሐማስ በእስራኤል ላይ ባለፈው መስከረም 26, 2016 ያደረሰውን ጥቃት ሰለባዎች እየዘከሩ፤ የብራንደንበርግ በር በርሊን ፣ ጀርመን
ሐማስ በእስራኤል ላይ ባለፈው መስከረም 26, 2016 ያደረሰውን ጥቃት ሰለባዎች እየዘከሩ፤ የብራንደንበርግ በር በርሊን ፣ ጀርመን

ሐማስ ባለፈው መስከረም በእስራኤል የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች በርካታ አጋሮቿ ቡድኑ ከተለያዩ ምንጮች የሚያገኘውን ገንዘብ ለማገድ እና የያዝያቸውን የጸረ-ሽብር ጥረቶች ለማጠናከር ዓለም አቀፍ ግብረ ኃይል ማቋቋማቸውን ዋሽንግተን በትላንትናው ዕለት አስታወቀች።

ግብረ ኃይሉ፣ ለሽብር ጥቃት ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ጋር እንዲሁም ከጉዳዩ ጋር የተዛመዱ የፋይናንስ መረጃ ልውውጦችን ለማጎልበት እና ሌሎች ተጨማሪ የትብብር ሥራዎችን መሥራት የሚያስችሉ ልምዶች እና ዕድሎች ዙሪያ እንደሚነጋገር የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት በመግለጫው አመልክቷል። መግለጫው አክሎም፣ “ግብረ ኃይሉ፣ የተባለውን ስጋት ለመቅረፍ፣ የፋይናንስና የደህንነት ክትትል በሚያደርጉ ክፍሎች፣ በመንግስት ተቋማት እና በግሉ ዘርፍ መካከል ያሉትን ግንኙነቶች ያጠናክራል” ብሏል።

ግብረ ኃይሉ ከአውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ኢስቶኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ እስራኤል፣ ሊክሸተንስታይን፣ ለግዘምበርግ፣ ኔዘርላንድስ፣ ኒውዚላንድ፣ ስዊዘርላንድ፣ ብሪታንያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና እንዲሁም ከሌሎች ክፍሎች የተውጣጡ የፋይናስ መረጃ አካላትን ያቀፈ ነው።

ሐማስ ባለፈው መስከረም 26, 2016 ባደረሰው ጥቃት 1,200 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታንያ እና አጋሮቿ በዋሽንግተን እና በሌሎች መንግስታት በአሸባሪነት የተፈረጀው ቡድን የሚያገኘውን የገንዘብ ምንጭ ለማድረቅ መንገድ ሲያፈላልጉ መቆየታቸው ይታወቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG