በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በዩናይትድ ስቴትስ


ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በኮቪድ-19 ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ግማሽ ሚሊዮን ሊደፍን መቃረቡን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል አመለከተ።

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ይህኑ አስመልክተው ዛሬ ማታ በዋይት ኃውስ ንግግር ያደርጋሉ፤ በማስከተልም የወረርሽኙን ሰለባዎች ለማሰብ የሻማ ማብራት እና የህሊና ጸሎት ሥነ ስርዓት ይከናወናል።

ዋናው የዩናይትድ ስቴትስ የተላላፊ በሽታዎች አዋቂው ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ ትናንት ለሲኤንኤን ቴሌቭዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ

“በሃገራችን ታሪክ በመተንፈሻ አካላት ህመም ይህን ያህል ሰው ያለቀበትን አስከፊ ምዕራፍ ወደፊት ለዘመናት ሲወሳ ይኖራል” ብለዋል።

ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣም በትናንት ዕሁድ ዕትሙ የፊት ገጽ ላይ አምስት መቶ ሽህ ነጥቦችን በመደርደር የወረርሽኙን ሰለባዎች አስቧል።

XS
SM
MD
LG