በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ከምርጫ ጋር የተያያዙ ሃሰተኛ መረጃዎችን በመዋጋት ላይ ናቸው


በአጋማሽ ዘመን ምርጫ መራጮች ድምጽ ለመስጠት ወረፋ ሲጠባበቁ፣ በማሪፓ ካውንቲ ኬቩ ክሪክ ከተማ አሪዞና፡፡
በአጋማሽ ዘመን ምርጫ መራጮች ድምጽ ለመስጠት ወረፋ ሲጠባበቁ፣ በማሪፓ ካውንቲ ኬቩ ክሪክ ከተማ አሪዞና፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ድምጽ ለመስጠት አሜሪካዊያን ከተሰለፉ ከሰዓታት በኋላ የድምጽ መቁጠሪያ ማሽኖቹ ላይ ብልሽቶች መከሰታቸውን ተክትሎ በርካታ የምርጫ ማጭበርበር አሉባልታዎች እና ክሶች እየተሰሙ ነው።

በማሪኩፓ፣ በአሪዞና፣ እና በመርሰር አውራጃ እና ኒው ጀርዚ ያሉ የምርጫ ጣቢያ ሃላፊዎች፤ አንዳንዶቹ ማሽኖች የምርጫ ካርዱን ለማንበብ ችግር አጋጥሟቸዋል ሲሉ አስታውቀዋል።

የማሪኮፓ አውርጃ የተቆጣጣሪዎች ቦርድ ሊቀመንበር ቢል ጌትስ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው ላይ ይህ ችግር በሀገሪቱ ያሉ 20 በመቶ የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ እክል መፍጥሩን ገልጸው “ችግሩን ለመቅረፍ እየሰራን ነው”ሲሉ አስታውቀዋል።

አያይዘውም የምርጫ መድገሚያ ቦታዎች እንዳሉና መራጮች ምርጫቸውን ቀጥለው ሲያበቁ ድምጻቸው በማሽኑ ውስጥ በተገጠሙ ደህንነታቸው በተጠበቁ ኮሮጆዎች ውስጥ የምርጫ ካርዳቸው እንደሚቆይ ገልጸዋል።

የመርሰር አውራጃ ባለሥልጣናት ተመሳሳይ ማሳሰቢያ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

“በሁሉም ቦታ የሚሰጡ የድምጽ መስጫ ኮሮጆዎች ደህንነቱ በተጠበቀ የምርጫ ቢሮ የጸጥታ ቦርድ እንዲቃኙ ተጠባባቂ ዕቅድ አዘጋጅተናል” ብለዋል።

በሁለቱም አጋጣሚዎች እክል የገጠማቸው ዶሚኒየን የምርጫ ስርዓት በተሰኘ ተቋም የተመረቱ የምርጫ ማሽኖች ናቸው። እነዚህ ማሽኖች ለረዥም ጊዜ በሃሰተኛ መረጃዎች ዘመቻ ሲካሄድባቸው ቆይቷል።

አንድ የሳይበር ደህንነት እና መሰረተ ልማት ኤጀንሲ (ሲአይኤስኤ) ከፍተኛ ባለስልጣን በተቋማቸው መመሪያ መሰረት ማንነታቸው ሳይገለጽ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡ ሲሆን “8800 የተለያዩ የምርጫ ክልሎች ሲኖሯቹ ጥቂት ችግሮች በየቦታው ያጋጥማሉ” ሲሉ ይህን መሰል ተግዳሮቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

አያዘውም “ጥቂቶቹን ችግሮች ከዚህ ቀደም በነበሩት ምርጫዎች ላይ አይተናቸዋል” ያሉ ሲሆን “ምንም ከተለመደው ውጪ የሆነ ነገር የለም” ብለዋል።

ይሁን እንጂ ይህን መሰል ማረጋገጫ ቢሰጥም ጉሩምሩምታዎች እና ውንጀላዎች በፍጥነት እየተሰራጩ ነው።

የምርጫ ተዓማኒነት ትብብሮች ጥምረት ተመራማሪዎች ትኩረታቸውን በምርጫ ደህንነት ላይ አድርገው በአሪዞና ግዛት የምርጫ ችግሮች ከታዩ በሁለት ሰዓት ጊዜ ውስጥ የተደረጉ 40000 የሚደርሱ ትዊቶችን መታዘብ ችለዋል።

“በማሪኮፓ አውራጃ ስለተከሰተው ነገር ሰዎች መታሰር አለባቸው። ይሄ ወንጀል ነው።” ሲል የወግ አጥባቂ ወጣቶች ቅስቀሳ ተቋም መስራች የሆነው ቻርሊ ኪርክ በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል።

በተመሳሳይ የአሪዞና የሪፐብሊካን የሃገረ ገዥ ተወዳዳሪ ካሪ ሌክ “ግራ እና ቀኝ ዘመሞች ወይም ራይኖዎች እንድትደናገጡ ነው የሚሹት። እቤታቹ እንድትመለሱ” ሲሉ ከሰዋል።

ይህን አባባል የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደግፈውታል። “የአሪዞናዎች ሆይ ድምጻችሁን ሳትሰጡ ከሰልፋቹ ለቃችሁ እንዳትወጡ” ሲሉ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የራሳቸው ማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ ላይ አስፍረዋል። ትራምፕ አክለውም “በተበላሹ ማሽኖች አማካኝነት እና ምርጫውን በማጓተት ምርጫውን ሊሰርቁ ነው። እንዳትፈቅዱላቸው!” ብለዋል።

የማሪኮፓ አውርጃ ታዲያ የአንዳንዶቹ ትዊተር ክሶች አጣጥለዋቸዋል። ኪርክ ታዲያ በሌላ ትዊተሩ “ከትዊተር ውስጥ ምንም ትክክለኝ አነገር የለም።”

የምርጫ ጣቢያዎቹ ወደ በኋላ ላይ ለችግሩ መፍትሄ ማግኘታቸውን እና ብልሽቱ በታየባቸው በሁሉም ጣቢያዎች ላይ አስፈላጊው መፍትሄ ተፈጻሚ እንደሚሆን በለጠፉት ጽሁፍ አስታውቀዋል።

ተመራማሪዎች እና የሳይበር ደህንነት ተቋማት ከምርጫ ቴክኖሎጂዎች ጋር ተያይዘው የሚነሱ የሃሰተኛ መረጃ ወጀቦች ተመሳሳይነት አላቸው ይላሉ።

"ኢንስኪት" የተሰኘ ቡድን ባልደረባ የሆኑ ግለሰብ በኢሜል በላኩት መረጃ መሰረት “አብዛኞቹ በዩናይትድ ስቴትስ የምርጫ ቴክኖሎጂ ማምርቻ ስርዓቶች ሃሰተኛ እና የተሳሳቱ መረጃዎች መነሻቸው በሃገር ውስጥ አስፈጻሚዎች አማካኝነት ነው” ሲሉ ጠቁመዋል።

ሌላው በዚህኛው ምርጫ አሳሳቢ የነበረው ነገር ደግሞ ጠበኛ ሰዎች ይህን በመሰሉ የተሳሳቱ መረጃ ተነሳስተው ወደ ግጭት ሊገቡ እንደሚችሉ የተለያዩ የግጭት ጥናቶች ማመላከታቸው ነው።

ማክሰኞ ዕለት እስከ እኩለ ቀን በነበረው የምርጫ ሂደትም በዩናይትድ ስቴትስ ይሄ አስከፊ የሆነ ስጋት የተቀረፈ ይመስላል።

XS
SM
MD
LG