በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የዝንጀሮ ፈንጣጣን ለመከላከል ተጨማሪ ዕርምጃ በመውሰድ ላይ ነች


የዝንጀሮ ፈንጣጣ (መንኪፖክስ) የምርመራ ውጤትን የሚያሳይ ናሙና
የዝንጀሮ ፈንጣጣ (መንኪፖክስ) የምርመራ ውጤትን የሚያሳይ ናሙና

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት የዝንጀሮ ፈንጣጣ (መንኪፖክስ) ለመከላከል ተጨማሪ ዕርምጃ በመውሰድ ላይ ናቸው።

ተጨማሪ ክትባቶችን እና እንደሚያቀርቡ የገለጹት ባለሥልጣናቱ ምርመራም በስፋት ማካሄድን ጨምሮ ሌሎችም ዕርምጃዎች በመውሰድ ሥርጭቱን ቀደም ብለው ለመከላከል እንደሚሞክሩ ገልጸዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እስካሁን በመዲናዋ በዋሽንግተን ዲሲ እና በሃያ ሰባት ክፍላተ ሀገር እስከትናንት ማክሰኞ ድረስ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተጠቁ 306 ሰዎች መገኘታቸው ተገልጿል።

በዓለም ዙሪያ ደግሞ አስቀድሞም በሽታው አብዝቶ የሚታይባቸውን የአፍሪካ አካባቢዎች ሳይጨምር ከአርባ በሚበልጡ ሀገሮች 4700 በበሽታው የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ታውቋል።

XS
SM
MD
LG