በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባይደን ረዳት በየመን ጉዳይ ከሳኡዲው ልኡል ይመክራሉ


ፎቶ ፋይል፦ የፕሬዚዳንት ባይደን የደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን
ፎቶ ፋይል፦ የፕሬዚዳንት ባይደን የደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን

የፕሬዚዳንት ባይደን የደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን በየመን ያለው የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቆምና የተኩስ አቁም ግፊት ለማድረግ ወደ ሳኡዲ አረብያ ሄደዋል፡፡

ሱሊቫን ከልኡል አልጋወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር በመገናኘት የመን ውስጥ በሳኡዲ አረብያን እና በየመን የሁቲ አማጽያን መካከል የተኩስ አቁም እንዲደረግ በሚቻልበት ሁኔታ ይነጋገራሉ ሲሉ ስማቸውን ያልገለጹ አንድ ባለሥልጣን ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡

ዛሬወደ ሳኡዲ የሚያቀኑት ሱሊቫን ወደ ሳኡዲ አረብያ የተጓዙ የጀመሪያው የባይደን አስተዳደር ከፍተኛው ባለሥልጣን ናቸው ተብሏል፡፡ በዋሽንግተን ፖስትጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ግድያ የሳኡዲው ልኡል እጃቸው ያለበት መሆኑን የሲአይኤ ሪፖርት ይፋ ካደረገ በኋላ ዋይት ሀውስ ከልኡሉ ጋር ያላው ግንኙነት በርቀት የተወሰነ መሆኑን ይታወቃል፡፡

XS
SM
MD
LG