በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሎምቦስ እና የአገሬው ሰዎች ቀን እየተከበረ ነው


የኮሎምበሰ ቀን ኦስቴን ቴክሳስ
የኮሎምበሰ ቀን ኦስቴን ቴክሳስ

ዩናዩትድ ስቴትስ በዛሬው እለት የኮሎምበሰ ቀን እና የአገሬው ሰዎች (Indigenous Peoples) ቀንን አክብራ ትውላለች፡፡ የኮሎሞበስ ቀን እኤአ በ1492 አሜሪካ ምድር ላይ ያረፈውን ክርስቶፈር ኮሎምበስን ለማሰብ ከ1971 ጀምሮ በየዓመቱ የሚከበር በዓል ነው፡፡

በምዕራቡ ንፍቀ ክበብ ውስጥ ወደ ሚኖሩ የአገሬው ተወላጆች አውሮፓውያኑ ያደረሷቸው ጥቃቶች፣ ያመጧቸው በሽታዎችና የስቃይ ዓይነቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተገለጡና እውቅና እያገኙ በመምጣታቸው በዓሉም በዚያ መንፈስ እየተቃኘ እንዲከበር የአገሬውም ሰዎች አብረው የሚታሰቡበትና የሚከበሩበት እንዲሆን መደረጉ ተመልክቷል፡፡

በዚህም መንፈሰ ባለፈው ዓርብ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በታሪክለመጀመሪያ ጊዜ ከኮሎምቦስ እለት ጋር የአገሬው ሰዎችም ቀን አብሮ እንዲከበር አዲስ አዋጅ አስነግረዋል፡፡

ባይደን በጻፉት አዋጃቸው “እኛ ዛሬ ብዙዎቹ አውሮፓውያኑ አሳሾች፣ በነባሮቹ የአገሬው ሰዎችና ነገዶች ላይ ያደረሱትን የሰቆቃ፣ የስህተት ታሪክና ግፍንም እንዲሁ እውቅና እንሰጠዋለን” ብለዋል፡፡ “እነዚህ አሳፋሪ የሆኑ የትላንትን ታሪኮቻችንን መደበቅና መቅበር የማንፈልግ መሆናችን የትልቅ አገርነታችን መለኪያ ነው፡፡ በሀቀኝነት እንጋፈጣቸዋለን ወደ ብርሃን እናመጣቸዋለን፣ ያስከተሏቸውን ችግሮችንም ለመቅረፍ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን” በማለትም ቃል ገብተዋል፡፡

”የአገሬው ሰዎች ቀን” በፌደራል ደረጃ እንዲከበር ባይደን ከማወጃቸው በፊት 11 ክፍለ ግዛቶች እለቱን ማክበ የጀመሩ ሲሆን የኦረገን ክፍለ ግዛትም ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው እለት ማክበርእንደሚጀሩ ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG