ዋሺንግተን ዲሲ —
የሰሜን ኮርያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺኦስ ሰን ሁይ ፕዮንግ ያንግና ዋሺንግተን በመጪው ቅዳሜ ተገናኝተው ለመነጋገር ተስማምተዋል ብለዋል። በዋዜማው “ቀዳሚ ግንኙነት” ይደረጋል ሲሉ አክለዋል። የስብሰባው ቦታ የት እንደሆነ ግልፅ አይደልም።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ዦንግ ኡን፣ ሁለቱን ኮርያዎች በሚለየው ከወታደራዊ ህልውና ነፃ በሆነው ቀጠና ተገናኝተው ከተነጋገሩ ሦስት ወራት በኋላ ነው በመጪው ቅዳሜም እንደሚገናኙ የተገልፀው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ