በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜን ኮሪያ ለአንድ ዓመት በእስር የቆየው አሜሪካዊ ማረፉ ተገለፀ


ሰሜን ኮሪያ ውስጥ ለአንድ ዓመት ተኩል በእስር ላይ የቆየው አሜሪካዊ የኮሌጅ ተማሪ ኦቶ ዋርምቢየር ትናንት ሰኞ ማረፉን ወላጆቹ ገለፁ።

ሰሜን ኮሪያ ውስጥ ለአንድ ዓመት ተኩል በእስር ላይ የቆየው አሜሪካዊ የኮሌጅ ተማሪ ኦቶ ዋርምቢየር ትናንት ሰኞ ማረፉን ወላጆቹ ገለፁ።

ወጣቱ ለረጅም ጊዜ ራሱን ስቶ በነበረት ሁኔታ ባለፈው ሳምንት ወደዩናይትድ ስቴትስ መላኩ ሲታወስ ኦሃዮ ክፍለ ግዛት ሲንሲናቲ ከተማ ያሉ ዶክተሮች የሃያ ሁለት ዓመቱ ወጣት ሰሜን ኮሪያ በቆየበት ወቅት አንጎሉ ላይ ከባድ ጉዳት አግኝቶታል ብለዋል። በምን ምክንያት እንደሆነ ግን ግልፅ አይደለም ።

ሰሜን ኮሪያ አሜሪካዊው ወጣት ከአንድ ሆቴል የፖለቲካ መግለጫ የያዘ ሰሌዳ በመስረቁ ተይዞ ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር እስራት ከፈረድበት ከጥቂት ቀናት በኋላ ራሱን ሳተ ብላለች።

የአጣዳፊ በምግብ መመረዝ ታሞ እንደነበርና የሚያስተኛ መድሃኒትም ተሰጥቶት እንደነበር ፒዮንግያንግ ገልፃለች። የኦቶ ወላጆች ይህን ምክንያት አይቀበሉም ልጃችን ሰሜን ኮሪያ ውስጥ የጭካኔ ተግባር ተፈፅሞበታል ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት ለቤተሰቡ ሃዘናቸውን ገልፀዋል። ልጅን እንደዚህ በደረሰ ዕድሜ ከማጣት የሚበልጥ ሃዘን አይኖርም ብለዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በሰሜን ኮሪያ ለአንድ ዓመት በእስር የቆየው አሜሪካዊ ማረፉ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:35 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG