በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከፍተኛ የሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣናት ኒውዮርክ ይገባሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሊያደርጉት ስለታቀደው ጉባዔ የሚወያዩ ከፍተኛ የሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣን ኒውዮርክ እንደሚገቡ ፕሬዚዳንቱ አረጋገጡ ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሊያደርጉት ስለታቀደው ጉባዔ የሚወያዩ ከፍተኛ የሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣን ኒውዮርክ እንደሚገቡ ፕሬዚዳንቱ አረጋገጡ ።

ሚስተር ትረምፕ ዛሬ በትዊተር ባወጡት ቃል “የሰሜን ኮሪያ ምክትል ሊቀመንበር ኪም ያንግ ቾል በአሁኑ ወቅት ወደ ኒውዮርክ እየተጓዙ ናቸው” ብለዋል።

ከዚህ የፕሬዚዳንቱ ቃል በሰዓታት ቀደም ብለው የወጡ የዜና ዘገባዎች የሰሜን ኮሪያ ገዢ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እና የቀድሞ የወታደራዊ ሥለላ ኃላፊ ኪም ዮንግ ቾል ቤጅንግ አውሮፕላን ማረፊያ እንደነበሩ ተናግረዋል። ነገ ረቡዕ ወደ ኒውዮርክ ለመብረር ዕቅድ ያላቸውን መሆኑን ደግሞ የደቡብ ኮሪያ የዜና አገልግሎት ዮንሃፕ ዘግበዋል።

ባለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንት ትረምፕ ለሰሜን ኮሪያው መሪ በላኩት ደብዳቤ

“በመግለጫዎ የገዘፈ ቁጣና ግልፅ ጠላትነት በማሳየትዎ ለሰኔ አሥራ ሁለት የተያዘው ጉባዔ የመቀመጣችን ዕቅድ ተሰርዟል” ማለታቸው ይታወሳል።

ሆኖም የሁለቱ ሀገሮች ድርድር ቀጥሎ ባለፈው ዕሁድ ከጦር ነፃው የኮሪያ ቀጣና ላይ ተነጋግረዋል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ በዛሬ የትዊተር መግለጫቸው ከሰሜን ኮሪያ ጋር ለምናካሂደው ንግግር ያደራጀነው ግሩም ቡድን በአሁኑ ወቅት ስለጉባዔው እየተነጋገረ ነው ብለዋል።

የዋይት ኃውስ ፅሕፈት ቤት ሹም ጆ ሃጊን እና ሌሎችም የትረምፕ አስተዳደር አባላት የሁለቱ መሪዎች ጉባዔ እንድታስተናግድ ወደታቀደችው ወደ ሲጋፖር ባለፈው ዕሁድ ተጉዘዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG