ዋሺንግተን ዲሲ —
ሰሜን ኮርያ ካለፈው ወር አንስታ ስድስት የአጭር ርቀት መች ቦልስቲክ ሚሳይሎችን ለሙከራ ተኩሳለች። ዩናይትድ ስቴትስና ደቡብ ኮርያ በህብረት ለሚያካሄዱት ወታደራዊ ልምምድ ምላሽ ነው ሲሉ የሰሜን ኮርያው መሪ ጆንግ ኡን ተናግረዋል። ሰሜን ኮርያ ወታደራዊ ልምምዱን አደጋ አድርጋ ታየዋለች።