በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማይክ ፖምፔዎ ከሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት ጋር እየተነጋገሩ ነው


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ዛሬ ኒውዮርክ ውስጥ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ቀኝ እጅ ከሆኑት ባለስልጣን ጋር መነጋገራቸውን ቀጥለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ዛሬ ኒውዮርክ ውስጥ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ቀኝ እጅ ከሆኑት ባለስልጣን ጋር መነጋገራቸውን ቀጥለዋል።

ውይይታቸው በሚቀጥለው ወር በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና በሰሜን ኮሪያው መሪ መካከል ሊካሄድ በሚችለው ስብሰባ ላይ ያተኮረ ነው።

ፖምፔዎ እና ኪም ዮንግ ቾል ያካሄዱት ውይይት በጣም በጥሩ ሁኔታ እየተከናውነ መሆኑን የተናገሩት ሚስተር ትረምፕ እሳቸውና ኪም ጆንግ ኡን መጀመሪያ ላይ በታቀደው መሰረት እአአ ሰኔ አሥራ ሁለት ቀን ይከናወናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

የሰሜን ኮሪያዎቹ ልዑካን ነገ ከኪም ጆንግ ኡን የተላከውን ደብዳቤ ይዘው ዋሺንግተን ይገባሉ ብለው እንደሚጠብቁም ሚስተር አመልክተው፣ የደብዳቤውን ይዘት ለማየት በጉጉት ላይ መሆናቸውን የዩናይትድ ስቴትሱ መሪ አክለዋል።

የሰሜን ኮሪያው መልዕክተኛ ኪም ዮንግ ቾል ባለፉት አሥራ ስምንት ዓመታት ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስን የጎበኙ የመጀመሪያ የዚያች ሃገር ከፍተኛ ባለሥልጣን መሆናቸው ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG