በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜን ኢትዮጵያ ጉዳይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የአፍሪካ ባለሥልጣናት


ብራያን ሀንት እና ኤሪክ ውድሃውስ
ብራያን ሀንት እና ኤሪክ ውድሃውስ

ህወሓት እና የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ሰላማዊ መፍትሔ የሚመጡ ከሆነ በግጭቱ ምክንያት የተዳከመውን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን ዩናይትድ ስቴትስ ገለጸች።

ፕሬዚዳንት ባይደን ከፈረሙት የማዕቀብ ትዕዛዝ ጋር በተያያዘ በመቀጠል ይወሰዳሉ ያሏቸውን እርምጃዎች አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የግጭቱ ተሳታፊ አካላት ወደ ድርድር የማይመጡ ከሆነ፣ የሚወሰደው የማዕቀብ እርምጃ ከተመረጡ ግለሰቦች እና ተቋማት ባለፈ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ህዝቦችን ዒላማ እንደማያደርግ የምስራቅ አፍሪካ እና የሁለቱ ሱዳኖች ተጠባባቂ ምክትል ረዳት ሚኒስትር ብራያን ሃንት ገልጸዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብዓዊ እና ሌሎች ድጋፎች እንደምትቀጥልም ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ ጉዳይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት የአፍሪካ ባለሥልጣናት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:28 0:00


XS
SM
MD
LG