በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒው ዮርኩ የዩናይትድ ስቴትስ ም/ቤት መቀመጫ ማሟያ ምርጫ ዲሞክራቱ ታም ሱዋዚ አሸነፉ


በኒው ዮርኩ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት መቀመጫ ማሟያ ምርጫ ዲሞክራቱ ታም ሱዋዚ አሸነፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:35 0:00

በኒው ዮርኩ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት መቀመጫ ማሟያ ምርጫ ዲሞክራቱ ታም ሱዋዚ አሸነፉ

ትናንት ማክሰኞ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት መቀመጫ ለመሙላት ኒው ዮርክ ውስጥ በተካሄደው ፉክክር ዲሞክራቱ ታም ስዋዚ አሸነፉ፡፡ ከኒው ዮርክ ከተማ ወጣ ብሎ ባለው የሁለቱም ፓርቲዎች ደጋፊዎች በሚገኙበት ወረዳ 3 ዲሞክራቱ ማሸነፋቸው ብርቱ ፉክክር እየተደረገበት ባለው በመጪው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ለፓርቲያቸው ተስፋ ሰጪ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ባለፈው ታሕሣስ የተባረሩት ሪፐብሊካኑ ጆርጅ ሳንቶስ የለቀቁትን መቀመጫ ለመሙላት በተካሄደው ልዩ ምርጫ ሪፐብሊካኗን ትውልደ አትዮጵያ ቤተ እስራኤል ማዚ ፒሊፕን ያሸነፏቸው ዲሞክራቱ ታም ስዋዚ “በአሁኑ ወቅት ምክር ቤቱን እየመሩ ላሉት ወዳጆቻችን መልዕክት አለን፡፡ ይልቅስ ለትረምፕ መሯሯጡን ትታችሁ ሀገራችሁን መምራት ጀምሩ” ብለዋል፡፡

ሱዋዚ ከአሁን በፊት ሦስት ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የኒው ዮርክ ወረዳ 3 ተወካይ ሆነው ማገልገላቸው ሲታወስ የትናንቱ ድላቸው ዳግመኛ ወደዋሽንግተን ይመልሳቸዋል። ሱዋዚ ሦስት ጊዜ ተመርጠው ካገለገሉ በኋላ ለግዛቷ አገረ ገዢነት ተወዳድረው የነበረ ሲሆን በዚያ አልተሳካላቸውም፡፡

የትናንቱ የታም ስዋዚ ድል በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ሪፐብሊካን ፓርቲው ያለውን ጠባብ የብዙሃን መቀመጫ ብልጫ ይበልጡን ያጠብበዋል፡፡

ማዚ ፒሊፕ በፉክክሩ መሸነፋቸውን ተቀብለው ትናንቱኑ ታም ሱዋዚን ስልክ ደውለው እንኳን ደስ ያለዎ እንዳሏቸው ገልጸዋል፡፡ የምርጫ ሂደቱን ለመከታተል ለታደሙት ደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ደግሞ “ አዎ ተሸንፈናል ነገር ግን በዚህ እናበቃለን ማለት አይደለም” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የተወለዱት ማዚ በአስራ ሁለት ዓመታቸው በ1983 እስራኤል ከጦርነቱ እና ከረሃብ ለማውጣት ወደ ሀገሯ ከወሰደቻቸው ከ14 ሺህ 500 ወደ ቤተ እስራኤላውያን ጋር ነው ወደእስራኤል የሄዱት፡፡ ካደጉም በኋላ በእስራኤል የመከላከያ ሓይሎች ውስጥ አገልግለዋል፡፡ ማዚ ፒሊፕ ዩክሬናዊ አሜሪካዊውን አግብተው በ1997 ኑሮአቸውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረጉ ሲሆን በ2014 የኒው ዮርክ ናሷ ወረዳ ምክር ቤት አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ዲሞክራቱ ታም ስዋዚ ያገኙት ድል በቅርብ ጊዜያት በተካሄዱ ምርጫዎች ሪፐብሊካኖች በሚያስገርም ሁኔታ ጠንከር እያሉ በመጡባት ኒው ዮርክ ከተማ ዳርቻ በምትገኘው በሎንግ አይላንድ አካባቢ ዲሞክራቶቹን እጅግ የሚያስፈልጋቸውን ድል አጎናጽፏቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪም ዲሞክራቶች የዩናይትድ ስቲትስ ምክር ቤትን ለመቆጣጠር እና ፕሬዚደንት ጆ ባይደንንም በድጋሚ ለማስመረጥ ለያዙት ጥረት ወሳኝ በመሆኑ በትላልቅ ከተሞች ዳርቻ የሚኖሩ ማህበረሰቦችን ጠንከር ያለ ድጋፍ ሊያገኙ እንደሚችሉ ተስፋ ይፈነጥቃል፡፡

የሪፐብሊካኗ ማዚ ፒሊፕ እና የዲሞክራቱ ታም ስዋዚ አጭር የምረጡን ዘመቻም በመጪው ምርጫ ትልቅ ትኩረት በሚይዙት እና የከተሞች ዳርቻ ወረዳዎች ፉክክር እንደሚወስኑ በሚጠበቁት በጽንስ ማስወረድ፡ በኢሚግሬሽን እና በወንጀልን ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ ነበር

ማዚ ፒሊፕ ራሳቸውም ፍልሰተኛ የነበሩ ሆነው ሳለ ወደ ኒዮርክ ከተማ የሚጎርፉትን ጥገኝነት ጠያቂዎች በሚመለከት ዲሞክራቶች እና ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የደቡቡባዊ ዩናይትድ ስቴትስ ድንበሮችን ማስከበር ያልቻላችሁ በማለት በተፎካካሪያቸው ታም ሱዋዚ ላይ ትችት አውርደውባቸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG