በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ከ50 ዓመታት በኋላ መንኮራኩር ወደ ጨረቃ አመጠቀች


‘ዩናይትድ ሎንች አላያንስ’ በተሰኘ የግል ኩባንያ የተገነባችው ‘ቨልካን ሴንቶር’ የተሰኘችው መንኮራኩር
‘ዩናይትድ ሎንች አላያንስ’ በተሰኘ የግል ኩባንያ የተገነባችው ‘ቨልካን ሴንቶር’ የተሰኘችው መንኮራኩር

አሜሪካ ከ50 ዓመታት በኋላ መንኮራኩር ወደ ጨረቃ ዛሬ ሰኞ አምጥቃለች፡፡ ዛሬ የመጠቀችውና ‘ቨልካን ሴንቶር’ የተሰነችው መንኮራኩር፣ ‘ዩናይትድ ሎንች አላያንስ’ በተሰኘ የግል ኩባንያ የተገነባች ሲሆን፣ በፈረንጆቹ አቆጣጠር የካቲት 23 ጨረቃ ላይ እንደምታርፍ ይጠበቃል።

እስከ አሁን ጨረቃ ላይ መንኮራኩር ያሳረፉ አገራት የተወሰኑ ሲሆኑ፣ በቅድሚያ በወቅቱ አጠራሯ ሶቪየት ኅብረት እ.አ.አ 1966፣ ቀጥሎም አሜሪካ ሲሆኑ። አሜሪካ አሁንም ጨርቃ ላይ ሰው ያሳረፈች ብቸኛ አገር ነች፡፡ ቻያን ባለፉት አሥርት ዓመታት ሦስት ግዜ መንኮራኩር ጨረቃ ላይ ስታሳርፍ፣ ህንድ ባለፈው ዓመት በሁለተኛ ሙከራዋ አሳክታለች፡፡ ዛሬ የመጠቀችው የአሜሪካ መንኮራኩር ሰው አልባ ስትሆን፣ አገሪቱ የሕዋ ፕሮግራሞቿን በግል ኩባንያዎች እንዲካሄዱ በማድረግ ላይ ነች፡፡

አዲሷን መንኮራኩር ለማምጠቅ ብሔራዊው የሕዋ ምርምር ተቋም (ናሳ) 100 ሚሊዮን ዶላር ማውጣቱ ታውቋል።

አንድ ሌላ ኮንትራት የተሰጠው ኩባንያም በመጪው ወር ሌላ መንኮራኩር ወደ ጨርቃ እንደሚያመጥቅ ታውቋል።

‘አርተሚስ’ የተሰኘው የናሳ ፕሮግራም፣ በአሥርተ ዓመቱ መጨረሻ ላይ የሰው ልጅን ወደ ጨረቃ ለመመለስና ቀጥሎም ኢላማውን ማርስ ለማድረግ በመሥራት ላይ መሆኑ ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG