በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ተደራዳሪዎች ወደ ታይዋን ተጉዘዋል


ፎቶ ፋይል፦ ታይፔይ
ፎቶ ፋይል፦ ታይፔይ

የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ተደራዳሪዎች በዚህ ሳምንት ወደታይዋን ተጉዘዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ተወካይ ቢሮ የቻይና ክፍል ምክትል የንግድ ተደራዳሪ ቴሪ ሜካርትን የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ወደታይፔይ የተጓዘው ለዋሽንግተን እና ለራስ ገዟ ደሴት በተወጠነው አዲስ የንግድ መርኃ ግብር ዙሪያ ድርድሩን ለመቀጠል መሆኑ ታውቋል።

የተወጠነው መርኃ ግብር ግብርና፣ ዲጂታል ንግድ፣ ሙስናን እና የአካባቢ ጥበቃን ጨምሮ 11 ክፍሎችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

ለሁለቱ ሀገሮች የተወጠነው የንግድ መርኃ ግብር ይፋ የተደረገው ባለፈው ሰኔ ወር ዩናይትድ ስቴትስ አውስትራሊያ ጃፓን እና ኒው ዚላንድ ጨምሮ ከእስያ ፓሲፊክ አካባቢ ሀገሮች ጋር አዲስ የኢኮኖሚ ትብብር ሥምምነት ካደረገች በኋላ ነው።

በዚያ ሥምምነት አንዳንድ ሀገሮች ቻይናን ያስቆጣል የሚል ሥጋት ስላሰሙ ታይዋን እንድትሳተፍ አልተጋበዘችም።

XS
SM
MD
LG