በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ሚሳየል መር አውዳሚ የጦር መርከብ የሱዳን ወደብን ጎብኝታለች


ፎቶ ፋይል፦ ዩ.ኤስ.ኤስ ዊንስተን ቸርችል የተባለችው ግዙፏ ሚሳየል መር አውዳሚ የጦር መርከብ
ፎቶ ፋይል፦ ዩ.ኤስ.ኤስ ዊንስተን ቸርችል የተባለችው ግዙፏ ሚሳየል መር አውዳሚ የጦር መርከብ

ሱዳን አሸባሪዎችን ከሚደግፉ መንግሥታት ዝርዝር ውስጥ በይፋ መሰረዟን ተከትሎ ከሦስት ዐስርት ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የዩናይትድ ስቴስት ባህር ኃይል በሱዳንን ወደብ ጉብኝት አድርጓል።

ዩ.ኤስ.ኤስ ዊንስተን ቸርችል የተባለችው ግዙፏ ሚሳየል መር አውዳሚ የጦር መርከብ ከትላንት በስቲያ ሰኞሱዳን ወደብ ስትደርስ የሱዳን ባለሥልጣናት እጅግ በጋለ እና በደስታ ስሜት የተቀበሏት ሲሆን፤ የሱዳን የባህርኃይል አዛዥ አልናሪ ሐሰን “የአሜሪካ ባህር ኃይል ጉብኝቱን ያደረገው በወሳኝ ወቅት ላይ ነው” ብለዋል።

የሱዳን እና የዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት ከተቋረጠ ከ30 ዓመት በኋላ ዩ.ኤስ.ኤስ ዊንስተን ቸርችልየተባለችውን ግዙፏ ሚሳየል መር አውዳሚ የጦር መርከብ ሱዳን ተቀብላ በማስተናገዷ በጣም ደስተኛ ናትብለዋል። ጉብኝቱ ታሪካዊ ነው እና ከፍተኛ አንደምታ አለው ካሉም በኋላ የሱዳን እና ዩናይትድስቴትስንዳግም ግንኙነት የሚወክል ነው ብለውታል።

ሱዳን በአውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር በ1990ዎቹ ከአልቃይዳ መሪ ጋር በተያያዘ አሸባሪዎችን በሚደግፉመንግሥታት ዝርዝር ውስጥ ተመዝግባ ለሦስት ዓስርት ዓመታት የቆየች ሲሆን፤ ባለፈው ታኅሣሥ ወርየቀድሞው ፕሬዚዳንት ትረምፕ አስተዳደር በወሰደው አቋም ከዚህ ዝርዝር ውስጥ እንድትወጣተደርጋለች። የባህር ኃይሉ ጉብኝትም በሱዳን ላይ የተጣለው ማዕቀብ ከተነሳ ከሁለት ወራት በኋላ የተደረገነው።

ሚሳየል መር አውዳሚ የጦር መርከቧን ይዘው ሱዳን የገቡት የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ መኮንኖች ሱዳንንየጎበኙ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ ከሱዳን ጋር “የወታደራዊ ለወታደራዊ ቁርኝት” ፍላጎት እንዳላትአንፀባርቀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ባህር ኃይል ስድስተኛ መርከብ ጉዳዮች ኃላፊ ሬየር አድሚራል ሚካኤል ባዜ የዩናይትድስቴትስ ፍላጎት ከሱዳን ጋር በትብብር መሥራት መሆኑን ገልፀዋል።

አያይዘውም “እዚህ የተገኘሁበት ምክኒያት ከእናንተ አገር የበለጠ ለመማር እና የባህር ኃይል ግንኙነቱንለማጠናከር ነው። በጣም ብዙ የምንጋራቸው እሴቶች አሉን። ሱዳን እና ሱዳን ሕዝቦች ዴሞክራሲንለማሻሻል ባሳዩት ለውጥ ኩራት ይሰማኛል። ይህንንም የምንደግፈው ጉዳይ ነው። ነገር ግን እኔ ዛሬ እዚህየተገኘሁበት ዋናው ምክኒያት ከባህር ኃይል ባልደረቦቻችን ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር ነው። ከዚህ አንፃር እጅለእጅ ተያይዘን የምናደርገውን ጉዞ እጠብቃለሁ” ብለዋል።

የአሜሪካ ባህር ኃይል ዩ.ኤስ.ኤስ ዊንስተን ቸርችል የተባለችው ግዙፏ ሚሳየል መር አውዳሚ የጦር መርከብይዞ ጉብኝት ያደረገው ቀደም ብሎ የገባው የሩሲያ የጦር መርከብ በሱዳን ወደብ ላይ ከቆመ በኋላ ነው።ሩሲያም የመጀመሪያው የባህር ኃይል ጣቢያዋን ለመገንባት የሱዳንን መንግሥት ፈቃድ እየጠበቀች ትገኛለችተብሏል።

(ዘገባው የናባ ሞሃዲን ነው)

የዩናይትድ ስቴትስ ሚሳየል መር አውዳሚ የጦር መርከብ የሱዳን ወደብን ጎብኝታለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:32 0:00


XS
SM
MD
LG