በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኮሪያና የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት፣ ከጦር እንቅስቃሴና መሣሪያ ነፃ ሥፍራ ተገናኘ

የሰሜን ኮሪያና የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት፣ ከጦር እንቅስቃሴና ከጦር መሣሪያ ነፃ በሆነው ሥፍራ ዛሬም ተገናኘው፣ ስለ መጭው የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና የፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ውይይት መነጋገራቸው ታወቀ።

የሰሜን ኮሪያና የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት፣ ከጦር እንቅስቃሴና ከጦር መሣሪያ ነፃ በሆነው ሥፍራ ዛሬም ተገናኘው፣ ስለ መጭው የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና የፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ውይይት መነጋገራቸው ታወቀ።

የስብሰባውን መሰረዝ ባለፈው ሐሙስ የተናገሩት ፕሬዚዳንት ትረምፕ፣ አሁን ደግሞ፣ «ሲንጋፖር ውስጥ ለመጪው ሰኔ ፭ ቀን የተያዘው ውይይት፣ በታቀደው መሰረት ይካሄዳል» ማለታቸው ተሰምቷል።

«ሰሜን ኮሪያ ብሩህ ተስፋ ያላት ሀገር እንደመሆኗ፣ አንድ ቀን ጠንካራ የኢኮኖሚና የምጣኔ ሀብት ሀገር እንደምትሆን በእርግጥ አምናለሁ» ሲሉ ትዊት ያደረጉት ፕሬዚዳንት ትረምፕ፣ «ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ደግሞ በእኔ ሃሳብ ይስማማሉ፤ እናም አንድ ቀን እውን ይሆናል» ብለዋል።

የሁለቱን መሪዎች የስብሰባ ዝግጅትና መሰናዶ ለመመልከት ወደ ሰሜን ኮሪያ የተጓዘውን ቡድን የሚመሩት፣ የቀድሞው በደቡብ ከሪያ የቀድሞው የus ልዩ መልዕክተኛ፣ አሁን በፊሊፒንስ የየዩናይትድ ስቴትስ አምባስደር በሆኑት በሱንግ ኡንመሆኑም ይታወቃል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG