በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሙስሊም አሜሪካውያን እንደሚመርጡ ይጠበቃል


ፎቶ ፋይል፡፦የባንግላዴሽ ተወላጅ የሆኑ ሙስሊም አሜሪካውያን በ2016ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በኒው ዮርክ ድምጽ ሲሰጡ
ፎቶ ፋይል፡፦የባንግላዴሽ ተወላጅ የሆኑ ሙስሊም አሜሪካውያን በ2016ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በኒው ዮርክ ድምጽ ሲሰጡ

ሙስሊም አሜሪካውያን ከአሜሪካ ህዝብ የሚወክሉት አንድ ከመቶ ያህሉ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የቪኦኤ ዘጋቢ ፋይዛ ቡካሪ እንደዘገበችው የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት በነገው እለት ለሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሙስሊሙ በነቂስ ወጥቶ ድምጹን እንዲሰጥ ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው፡፡

መምረጥ ከሚችሉ ሙስሊም አሜሪካውያን መካከል፣ 78 ከመቶ የሚሆኑት፣ በነገው እለት በሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ፣ ተመዝግበዋል፡፡ በማህበረሰብ ፖሊሲና መግባባት ተቋም አማካይነት፣ ከሙስሊም አሜሪካውያን፣ የተሰበሰበው የህዝብ አስተያየት ድምጽ እንደሚያሳየው፣ በ2016 ከነበረው የ60 ከመቶ ጋር ሲነጻጸር አሁን የተመዘገበው 78 ከመቶ ትልቅ እመርታ ነው፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ መስጂዶች፣ የመራጮችን ንቃት በማሳደግ ፣ ከፍተኛውን ድርሻ መጫወታቸው ተነግሯል፡፡ በዚህ ረገድ በቨርጂኒያ የሚገኘው የአደምስ ማዕከል በአሜሪካ ከሚገኙ ትላልቅ የእስልምና ማዕከላት አንዱ ነው፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች በርከታ ሙሲሊም መራጮችን ግንዛቤ አሳድጎ በማንቀሳቀስ ይታወቃል፡፡ ይህን ከሚያደርግባቸው መንገዶች አንዱ የአዳምስ ሲቪክ ኤንጌጅመት ግሩፕ ወይም የአዳምስ የዜጎች ተሳትፎ ቡድን የመሳሰሉትን ተቋማትን በማቋቋም ነው፡፡ ይህን ተቋም በምትክል ሊቀመንበርነት የሚመሩት ሰይድ አሽራፍ እንዲህ ይላሉ

"እስካለፈው ሳምንት መጨረሻው እስከ ምርጫው መቃሪቢያ ድረስ፣ ሰዎች አስቀድመው እንዲመርጡ ስንቀስቀስ ነበር፡፡ የሚሰጡት ድምጽ በአሜሪካ ዴሞክራሲ ላይ ተጨማሪ ድምጽ መሆኑን እንዲረዱት እያደረግን ቆይተናል፡፡"

አሽራፍ እንደሚሉት የአደምስ ማዕከል ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ ዓላማውም የተወሰነው ወገን ወይም እጩ ለማስመረጥ ሳይሆን ዜጎች የመምረጥ መብታቸውን ተጠቅመው በምርጫው እንዲሳተፉ የምርጫውን አስፈላጊነት እንዲማሩ ለማድረግ ነው፡፡ ከሙስሊም ተቋማት በተጨማሪ በመላው ዩናይትድ ስቴት የሚገኙ ሌሎች ገለልተኛ የሆኑ ተቋማትም በፖለቲካውም ረገድ ቢሆን የማህበረሰቡ አባላት ሊያመጡ የሚችሉትን ተጽእኖ በማስገነዝብ ሙስሊም አሜሪካውያንን የሚቀሰቅሱ ተቋማትም አሉ፡፡ ከአሜሪካ ሙስሊም ተቋም ወይም (አሜሪካን ሙስሊም ኤንስቲቱሽን) ድሬክተር የሆኑት ሻኺድ ረህማን እንዲህ ይላሉ

“በጉዳዩ ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶች እንደሚሉት በአሜሪካ ይገኛሉ ከሚባሉት ሙስሊሞች መካከል ከሶስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት በዘንድሮው ምርጫ ድምጻቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይገመታል፡፡”

በጉዳዩ ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶች እንደሚሉት፣ በአሜሪካ ይገኛሉ ከሚባሉት ሙስሊሞች መካከል፣ ከሶስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት፣ በዘንድሮው ምርጫ ድምጻቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይገመታል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሙስሊም አሜሪካውያን እንደሚመርጡ ይጠበቃል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:23 0:00


XS
SM
MD
LG