በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞደርና ክትባቱ ለህጻናትም የሚሰራ መሆኑን አስታወቀ


ፎቶ ፋይል፦ የጤና ባለሞያዋ የሞደርና ክትባት ሲሰጡ
ፎቶ ፋይል፦ የጤና ባለሞያዋ የሞደርና ክትባት ሲሰጡ

የዩናይትድ ስቴትስ መድሃኒት አምራች ሞደርና ትናንት ረቡዕ ባወጣው መግለጫ የኮቪድ-19 ክትባቱ ለህጻናት፣ ለሚድሁ ልጆችና፣ መዋለ ህጻናት ለሚውሉ ልጆች የሚሠራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የሞደርና ፕሬዚዳንት ስቴፈን ሆግ እንዲህ ብለዋል፣

“ዛሬ በሁለቱ ዙር የኮቪድ-19 ክትባት መድሃኒታችንን የምናስታውቀው ዕድሜያቸው ከ6 ዓመት በታች በሆኑ በአምስት ሺሕ ህጻናት ላይ በተሞክረውና በሦስተኛ ዙር ከተደረገ የጥናት ውጤት በመነሳት ነው፡፡

አስደሳቹ ዜና የጥናቱን ቀዳሚ ምዕራፍ አሟልተናል፡፡ ይህ ማለት የፀረ ኮቪድ-19 ክትባቱ ልክ በአዋቂዎች ላይ እንደሚሰራው ሁሉ ልጆችም በተመሳሳይ ይሰራል ማለት ነው፡፡

ተቆጣጣሪዎቹ አካላት የሚስማሙ ከሆነ፣ አነስተኛው መጠን የክትባት መድሃኒት በቂና ውጤታማ ነው፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ በቀጣዩ የበጋ ወቅት ትናንሾቹን ህጻናት ማስከተብ ለመጀመር እድል ይሰጣል ተብሏል፡፡

ሞደርና በቀጣዩ ሳምንታት ክትባቶቹን በዩናይትድ ስቴትስና በአውሮፓ ለሚገኙ አስፈጻሚ ባለሥልጣናት ለውሳኔ እንደሚያቀርብ አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG