በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ሰላም አስከባሪ ጦር በማሊ የሚያደርገውን በረራ ለጊዜው አቋረጠ


ፎቶ ፋይል - የባማኮ አውሮፕላን ማረፊያ እአአ ማርች 5/2021
ፎቶ ፋይል - የባማኮ አውሮፕላን ማረፊያ እአአ ማርች 5/2021

በማሊ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ጦር ወደ ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ማሊ የሚያደርገውን በረራ ለጊዜው ሙሉ ለሙሉ ማቁረጧን የገለጸ ሲሆን፣ የአውሮፓ ህብረት ደግሞ በማሊ የአየርና የየብስ ትራንስፖርት ላይ ማዕቀብ ማስተላለፉን አስታውቋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትናትን እሁድ ለሠራተኞች ባስተላለፈው የኢሜልይ መልዕክት ሁሉም በረራዎች ላልተወሰነ ጊዜ የተቋረጡ መሆኑን ገልጾ ከማሊ መንግሥት ባለሥልጣናት ማረጋጋጫ ሲገኝ በረራዎቹን እንደገና እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት ብዙዎቹ በረራዎች የሚደረጉት በማሊ ዋና ከተማና ከማዕከል ወደ ሰሜን የአገሪቱ ክፍሎች ወደ ሚገኙ ከተሞች መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በመፈንቅ ለመንግሥት ሥልጣን የጨበጠው የማሊ ወታደራዊ መንግሥት በዚህ ዓመት አካሂደዋለሁ ያለውን ምርጫ ወደ አምስት ዓመት በማስተላለፉ በርካታ የምዕራብ አፍሪካ አገሮች ማሊ ላይ ማዕቀብ የጣሉ መሆናቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

የቀድሞ ማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም አቡባካር ኬይታ አካ
የቀድሞ ማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም አቡባካር ኬይታ አካ

በመፈንቅለ መንግሥቱ ከሥልጣን የተወገዱት የቀድሞ ማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም አቡባካር ኬይታ አካ ትናንት እሁድ በ76 ዓመታቸው ባማኮ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ሮይተርስ የሳቸው የቀድሞ የፍትህ ሚኒስትር የነበሩት ጠቅሶ እንደዘገበው እኤአ ነሀሴ 18/2020 ከሥልጣናቸው በመፈንቅለ መንግሥት የተወገዱት የማሊው በምን ምክንያት እንደሞቱ እስካሁን ኣለመታወቁም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG