በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሠራዊት እርዳታ ሰጪ ሄሊኮፕተሮችን በጃፓን ሊያሰማራ ነው


በጃፓን ምዕራባዊ የባሕር ዳርቻ በሚገኘው የኖቶ ባሕረ ገብ መሬት በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ የወደመውን ሥፍራ ተከልሎ ይታያል፣ በዋጂማ፣ ኢሺካዋ ግዛት፣ ጃፓን፣ እአአ ጥር 2024
በጃፓን ምዕራባዊ የባሕር ዳርቻ በሚገኘው የኖቶ ባሕረ ገብ መሬት በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ የወደመውን ሥፍራ ተከልሎ ይታያል፣ በዋጂማ፣ ኢሺካዋ ግዛት፣ ጃፓን፣ እአአ ጥር 2024

ዩናይትድ ስቴትስ በጃፓን ምዕራባዊ የባሕር ዳርቻ በሚገኘው የኖቶ ባሕረ ገብ መሬት በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከተቀረው የሃገሪቱ ክፍል ተቆርጠው የቀሩትን የአካባቢው ነዋሪዎች ለመድረስ ሁለት ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮችን እንደምታሰማራ በቶኪዮ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ዛሬ አስታወቁ።

አምባሳደር ራም ኢማኑኤል ቀደም ሲል ትዊተር ይባል በነበረው የማኅበራዊ ሚድያ መድረክ ‘ኤክስ’ አማካኝነት ባስተላለፉት መልዕክት እንዳስረዱት ዩናይትድ ስቴትስ የምታሰማራቸው ሁለቱ ‘ብላክሃክ’ ሄሊኮፕተሮች አስፈላጊ የዕርዳታ ቁሳቁሶችን እና ሠራተኞችን በማጓጓዝ በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት በአካባቢው የተሰማሩትን የጃፓን የጦር መርከቦች ያግዛሉ።

በተያያዘ ዜና የጃፓኑ የመከላከያ ሚኒስትር ሚኖሩ ኪሃራ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፣

“ለረድኤት ሥራ የሚሰማሩት የዩናይትድ ስቴትስ አውሮፕላኖች በነገው ዕለት ሥራ ይጀምራሉ” ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ እርዳታ በቀጣዮቹ ቀናት ውስጥ ከዚህም ሊሰፋ እንደሚችል ተጠቅሷል።

ከ220 በላይ ሰዎችን የገደለው፣ በሺዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶች እና እንዲሁም የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ጨምሮ በርካታ መሰረተ ልማቶችን ያወደመው በአውሮፓውያኑ አዲስ ዓመት የመጀመሪያ ቀን የደረሰው አደገኛ ርዕደ መሬት በአደጋው የተመታውን ባሕረ ገብ መሬት ከተቀረው የጃፓን ክፍል ጋር የሚያገናኙ አውራ ጎዳናዎችን ከማፈራረሱ ባሻገር ለአደጋ የተጋለጡ ሰዎችን በባሕር ማጓጓዝም አዳጋች ያደረገ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG