በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ለሁቲ አማጺያን ሊላኩ የታቃዱ ጦር መሳሪያዎችን ያዘ


የዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል ኢራን-ሰር የሆኑ ሚሳይሎች እና የሌሎች ጦር መሣሪያ ክፍሎች የተካተቱበት ለየመን ሁቲ አማፅያን ሊላክ የታቀደ ወታደራዊ ቁሳቁስ በቁጥጥር ስር አውለዋል፤ እአአ ጥር 16/2024
የዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል ኢራን-ሰር የሆኑ ሚሳይሎች እና የሌሎች ጦር መሣሪያ ክፍሎች የተካተቱበት ለየመን ሁቲ አማፅያን ሊላክ የታቀደ ወታደራዊ ቁሳቁስ በቁጥጥር ስር አውለዋል፤ እአአ ጥር 16/2024

የዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል ኢራን-ሰር የሆኑ ሚሳይሎች እና የሌሎች ጦር መሣሪያ ክፍሎች የተካተቱበት ለየመን ሁቲ አማፅያን ሊላክ የታቀደ ወታደራዊ ቁሳቁስ በቁጥጥር ስር አውለዋል።

በዚያ ባለፈው ሳምንት በተደረገ ወታደራዊ አሰሳ ወቅት: ሁለት የባሕር ኃይሉ ልዩ ኮማንዶ አባላት የደረሱበት ያለመታወቁም ተገልጧል።

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ መግለጫ በዛሬው ዕለት ይፋ እንዳደረገው፡ ይህ የዩናይትድ ስቴትስ ባሕር ኃይል እና አጋሮቹ በቁጥጥር ሥር ያዋሉት ወታደራዊ ቁሳቁስ፡ በቀይ ባሕር በሚተላለፉ መርከቦች ላይ ተከታታይ ጥቃቶች በመሰንዘር በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ አደጋ ለደቀኑት የሁቲ አማጺያን ለማድረስ ታቅደው ከተያዙ የጦር መሳሪያ ጭነቶች የቅርብ ጊዜው ነው። አማጽያኑ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በሃማስ ላይ በከፈተችው ጦርነት ላይም ከአደን ባሕረ ሰላጤ የሚነሱ ተመሳሳይ ጥቃቶችን መሰንዘራቸው ይታወቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ ቀይ ባሕር ላይ አማጽያኑ የፈጸሙት ሳይሆን አይቀርም የተባለ አዲስ ጥቃት መጠነኛ አደጋ ማድረሱን፣ ነገር ግን የመቁሰል አደጋ የደረሰበት ያለመኖሩን ባለ ስልጣናቱ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG