በየመን ሁቲ አማፂያን የተተኮሱ ቦልስቲክ ሚሳይሎች፣ በቀይ ባህር ላይ ሶስት የንግድ መርከቦችን መምታታቸውን እና፤ ለሰዓታት በዘለቀው ጥቃት የአሜሪካ የጦር መርከብ እራሱን ለመከላከል ባደረገው ጥረት ሦስት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖችን) መቶ መጣሉን የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አስታወቀ።
በኢራን የሚደፉት የሁቲ አማፂያን ለሁለቱ ጥቃቶች ሀላፊነት ወስደዋል።
ጥቃቱ፣ ከእስራዔል እና ከሐማስ ጦርነት ጋር በተገናኘ በመካከለኛው ምስራቅ የሚደረጉ የባህር ላይ ጥቃቶች መባባሳቸውን ያመለከተ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ፣ በተለይ ኢራንን ተጠያቂ ለማድረግ "ሁሉንም አይነት ተገቢ ምላሽ ግምት ውስጥ እንደምታስገባ" ቃል ገብታለች።
የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ ባወጣው መግለጫ "እነዚህ ጥቃቶች ለዓለም አቀፍ ንግድ እና የባህር ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ናቸው" ያለ ሲሆን በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ ሀገሮችን የሚወክሉ ዓለም አቀፍ ሠራተኞችን ሕይወት አደጋ ላይ መጣላቸውንም አመልክቷል።
"እነዚህ ጥቃቶች የመን በሚገኘው የሁቲ አማፂያን ቢሰነዘሩም፣ ሙሉ ለሙሉ በኢራን መደገፋቸውን የምናምንበት በቂ ምክንያት አለን" በማለትም አክሎ ገልጿል።
ማዕከላዊ ዕዙ እንዳስታወቀው አንድነት የተሰኘው መርከብ በጥቃቱ መጠነኛ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፣ ቁጥር ዘጠኝ እና ሶፊ ሁለተኛ የተሰኙ፣ የፓናማ ባንዲራ የሚያውለበልቡ ሁለት የንግድ መርከቦችም እንዲሁ በሚሳይል ተመተዋል።
መድረክ / ፎረም