በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የሁቲዎቹን አምስት አብራሪ አልባ አውሮፕላኖች አውድመናል” የዩስ የጦር ኅይል


የመን ካርታ
የመን ካርታ

የዩናይትድ ስቴትስ እና የጥምረቱ ኅይሎች ትናንት ማክሰኞ ማታ ቀይ ባሕር ላይ የሁቲዎቹን አማጽያን አምስት አብራሪ አልባ አውሮፕላኖች ማውደማቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ አስታወቀ፡፡
ኢራን የምትደግፋቸው ሁቲ አማጽያን ከሚቆጣጠሯቸው የየመን አካባቢዎች የተነሱት አውሮፕላኖች በቀይ ባሕር አካባቢ ባሉ የንግድ መርከቦች የዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኅይል እና የጥምረቱ መርከቦች ላይ አደጋ ደቅነው እንደነበረ የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ ገልጿል፡፡
የትናንቱ እርምጃ በቀይ ባሕር በሚተላለፉ መርከቦች ላይ ሁቲዎች የሚያደርሱትን ጥቃት ለማስቆም ባለፉት ወራት ሲካሄድ የቆየውን ጥቃት የተከተለ ነው፡፡ ሁቲ አማጽያኑ መርከቦች ላይ ጥቃት የምናደርሰው ጦርነት ላይ ባለችው ጋዛ ላሉት ፍልስጥኤማውያን ድጋፋቸውን ለመግለጽ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG