በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሃይል ከሶማሊያ ወታደሮቹን የማስወጣት እንቅስቃሴ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሃይል ሶማሊያ ውስጥ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሃይል ሶማሊያ ውስጥ

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሃይል ከሶማሊያ ወታደሮቹን የማስወጣት እንቅስቃሴውን ማጠናቀቁን አስታወቀ።

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሃይል የአፍሪካ ዕዝ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ክሪስቶፈር ካርንስ ለቪኦኤ የሶማሊኛ ክፍል በሰጡት ቃል ወታደሮቹ በአውሮፓ አቆጣጠር እስከዚህ ጥር አጋማሽ በነበረው ጊዜ ወታደሮቹን አስወጥተን እንድናጠናቅቅ በታህሳስ ወር ፕሬዚደንታዊ መመሪያ ተላልፎልን ነበር፤ ከተሰጠን የጊዜ ገደብ አስቀድመን አከናውነናል ሲሉ አረጋግጠዋል።

ቁጥራቸው ከስድስት መቶ ሃምሳ እስከ ስምንት መቶ የሚደርሱት አሜሪካውያን ወታደሮች ለሶማሊያ የጥር ሰራዊት ድጋፍ በመስጠትና ዳናብ ወይም መብረቁ የተባለውን ልዩ ብርጌድ በማሰልጠን ሲረዱ መቅይተቸው ታውቋል። በጣም ጥቂት ወታደሮች ሶማሊያ ውስጥ እንደሚቆዩ የአፍሪኮም ቃል አቀባዩ ጨምረው አስረድተዋል።

XS
SM
MD
LG