ወደ ካልፎርንያ የአየር ኃይል መሠረት ሲያመራ የነበረ አንድ የአሜሪካ ወታደራዊ ጄት ኒው ሜክሲኮ ግዛት ውስጥ ትላንት ማክሰኞ ተከስክሷል።
በአደጋው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል የተባለው አብራሪ በሕክምና ላይ እንደሚገኝም ታውቋል።
በጄቱ ውስጥ የነበረው አብራሪው ብቻ እንደነበርና ከአልበከርኪ ከተማ አየር ማረፊያ ወጣ ብሎ በሚገኝ ተራራማ ሥፍራ መከስከሱን የከተማዋ የእሳት አደጋ አገልግሎት አስታውቋል።
ጄቱ ኒው ሜክሲኮ በሚገኘው ኪርትላንድ የአየር ኃይል መሠረት ነዳጅ ሞልቶ ከተነሳ በኋላ መከስከሱን የጄቱ አምራች የሆነው ሎክሂድ ማርቲን ኩባንያ ቃል አቀባይ ለአሶስዬትድ ፕረስ ዜና ወኪል በኢሜይል አስታውቀዋል።
ከሁለቱም የአየር ኃይል መሠረቶች ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ያልተቻለ ሲሆን፣ አደጋው በምርመራ ላይ መሆኑ ታውቋል።
መድረክ / ፎረም