ከዩናይትድ ስቴትስ ለጋዛ የተላከው የመጀመርያው የሰብአዊ ርዳታ በአሜሪካ የጭነት መርከብ ተጭኖ ትላንት ሐሙስ ከቆጵሮስ ተነስቷል።
ስጋሞር በተባለው መርከብ የተጫነው ርዳታ ወደሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ መርከቦች ከመጋባቱ በፊት በጋዛ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በዩናይትድ ስቴትስ ባህሩ ላይ ወደ ተገነባው ማከማቻ ስፍራ ይጓዛል፡፡
አዲስ የተገነባው ስፍራ ለጋዛ ህዝብ ህልውና ወሳኝ የሆኑ እርዳታዎችን በየቀኑ ለበርካታ የጭነት መኪናዎች በማቅረብ የእርዳታ አሰጣጥን በእጅጉ እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።
ዋናው የራፋህ ድንበር መሻገሪያ አሁንም ዝግ በመሆኑ አስፈላጊው ምግብ እና ውሃ ጨምሮ የሚያስፈልገውን አስቸኳይ ርዳታ በዚህ በኩል ማስተላለፉ አስፈላጊ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የብሩኪንግስ ተቋም የመከላከያ ተንታኝ ሚካኤል ኦሃንሎን በጋዛ ሁለት ሚሊዮን ነዋሪዎች በረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸው አስከፊ አደጋ መሆኑን በመግለጽ፣ ይህ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በጣም አሳሳቢ ከሆኑት የምግብ ቀውሶች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡
መድረክ / ፎረም