በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይል ሶማሊያ ውስጥ በአልሸባብ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት አደረሰ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይል ሶማሊያ ውስጥ በአብራሪ አልባ አውሮፕላን ባካሄደው ጥቃት ከአንድ መቶ በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች መግደሉን የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ አስታወቀ።

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይል ሶማሊያ ውስጥ በአብራሪ አልባ አውሮፕላን ባካሄደው ጥቃት ከአንድ መቶ በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች መግደሉን የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ አስታወቀ።

ትናንት ማክሰኞ የተካሄደው ጥቃት ከሶማሊያ ዋና ከተና ከሞቃዲሾ ሁለት መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ቤይ ክፍለ ግዛት የአልሸባብ ተዋጊ ማሰልጠኛ ካምፕ መደብደቡን የዕዙ ባለሥልጣናት ለቪኦኤ ገልፀዋል።

የአፍሪኮም ቃል አቀባይ ሌተና ኮማንደር አንተኒ ፍላቪዮ በቦታው የነበሩት ታጣቂዎች እንደነበሩ በግልፅ ተመልክተናል ብለዋል።

የአየር ጥቃቱ የተካሄደው ከሶማሊያ መንግሥት ጋር ተቀናጅቶ መሆኑን ያስታወቀው የዩናይትድ ስቴትስሱ የጦር ኃይል ዓላማውም ሶማሊያ በግዛትዋ ውስጥ ያሉዋትን ስጋቶች እንድታስወግድ ለመርዳት እና በዓለም ዙሪያ የሽብር ጥቃቶችን ለማካሄድ ሴራ ለማቀድ ሊውሉ የሚችሉ ምሽጎችን ለመደምሰስ መሆኑን አመልክቷል።

ዩናይትድ ስቴትስ እአአ 2017 ውስጥ እስካሁን በአልሸባብ ላይ ወደሠላሳ የሚደርሱ ጥቃቶችን አካሂዳለች። በዚህ የአውሮፓዋያን ህዳር ወር ብቻ ከሥድስት በላይ ጥቃቶች አድርሳለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG