በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ ሠራዊት ውስጥ የኮቪድ-19 ተጋላጮች ቁጥር ቀንሷል


ፎቶ ፋይል፦ የሠራዊቱ የጤና ባለሞያዎች ሚያሚ፣ ፍሎሪዳ
ፎቶ ፋይል፦ የሠራዊቱ የጤና ባለሞያዎች ሚያሚ፣ ፍሎሪዳ

አብዛኞቹ የሠራዊቱ አባላት በመከተባቸው ባላፈው ወር ውስጥ በዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሠራዊት አባላት መከካል የኮቪድ-19 ተጋላጮች ቁጥር መቀነሱን የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ፡፡

በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ 4ሺ 902 የነበረው የተጋላጮች ቁጥር በዚህ ሳምንት ወደ 863 ወርዷል፡፡ ይህ ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ የመጀመሪያው ዝቅተኛ ቁጥር ሲሆን፣ ሁሉም የሠራዊቱ አባል እንዲከተብ የተቀመጠው ቀነ ገደብ ከመድረሱ በፊት የተገኘ ውጤት መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን ባለፈው ነሀሴ ሁሉም የሠራዊት አባላት በተሰጠው ቀነ ገደብ እንዲከተብ ካለበለዚያ ብርቱ ቅጣት ይጠብቀዋል የሚል ትዕዛዝ ያወጡ መሆኑ ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG