በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናየትድ ስቴትስ ጦር ኒዠር ውስጥ ሦስት ወታደሮቹ እንደተገደሉበት አስታወቀ


ምዕራብ አፍሪካዪቱ ኒዠር ውስጥ ሦስት ወታደሮቹ እንደተገደሉበት የዩናየትድ ስቴትስ ጦር አስታወቀ።

ምዕራብ አፍሪካዪቱ ኒዠር ውስጥ ሦስት ወታደሮቹ እንደተገደሉበት የዩናየትድ ስቴትስ ጦር አስታወቀ።

ወታደሮቹ የተገደሉት በአሜሪካና ኒዥር ጥምር የቅኝት ኃይል ላይ ትናንት ጥቃት አደጋ በተጣለበት ጊዜ እንደነበር ተገልጿል።

በጥቃቱ የየትኛው ሃገር ዜጋ እንደሆነ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የአፍሪካ ዕዝ ሳይገልፅ “አንድ ሌላ የአጋር ሃገር ወታደርም ተገድሎብናል” ብሏል። ሌሎች ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች ቆስለዋል።

ለዚህ ከዋና ከተማዪቱ ኒያሜ 200 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ኒዠር ከማሊ ጋር በምትዋሰንበት አካባቢ በሚገኝ ሥፍራ ለተፈፀመው ጥቃት ኃላፊነት የወሰደ የለም።

ኒዠር በምሥራቅ ከናይጀሪያው ቦኮ ሃራም፤ በምሥራቅ አልጀሪያ ላይ ከሸመቀው አልቃይዳ በእሥላማዊ ማግሬብ የሽብርና የሁከት ቡድኖች ጋር በምታካሂዳቸው ውጊያዎች ውስጥ ለማገዝ አነስተኛ ቁጥር ያለው የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ላለፉት አራት ዓመታት እዚያ ተሠማርቶ ይገኛል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG