በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይል በሶማሊያ አልሻባብ ላይ የአየር ጥቃት አደረሰ


ቄይካድ ሶማሊያ

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሃይል በሶማሊያ የአልሻባብ ታጣቂዎች ላይ በድጋሚ የአየር ጥቃት ማካሄዱን አረጋግጧል። ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሦስተኛው የአየር ጥቃት መሆኑ ነው።

በማዕከላዊ ጉልሙዱድ ክፍለ ግዛት ቄይካድ በሚባል አካባቢ ትናንት ዕሁድ የአየር ጥቃት የተፈጸመው የሶማሊያ መንግሥት ኃይሎችን ለማገዝ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይል አስታውቋል።

ቀደም ብሎ የሶማሊያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ የአየር ጥቃቱ የተካሄደው የፌደራል ኃይሎች እና በዩናይትድ ስቴትስ የሰለጠኑ ወታደሮች ከታጣቂዎቹ ጋር እየተዋጉ ባሉበት አካባቢ መሆኑን አስታውቆ ነበር ፥ ሆኖም የቆሰሉ ወይም የተገደሉ ታጣቂዎች ስለመኖራቸው በዝርዝር አልተገለጸም።

የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ በዚህ ጥቃት አልሻባብ በሶማሊያ መንግስት ላይ ጥቃት የመሰንዘር አቅም በከባዱ ተመቷል ብሏል።

አስተያየቶችን ይዩ (1)

XS
SM
MD
LG