በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ ደቡባዊ የድንበር ክፍለ ግዛት የፍልሰተኞች ሁኔታ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በዩናይትድ ስቴትስ ደቡባዊ የድንበር ክፍለ ግዛት ቴክሳስ የፍልሰተኛ ማቆያ ማዕከሎች ከባድ የሆነ ለተራዘመ ጊዜ የማቆየት እና በሰው ብዛት የመጨናነቅ ችግር መኖሩን ባለፈው ሳምንት የአገር ደኅንነት ሚኒስቴር ዋና ተቆጣጣሪ (ኢንስፔክተር ጀነራል) አጉልተው አስገንዝበዋል።

ከዚያ ወዲህ የወጣ አንድ አዲስ ሪፖርት ደግሞ በአሪዞና ክፍለ ግዛትም በሚገኙ ማቆያ ጣቢያዎች የተያዙ ፍልሰተኛ ልጆች ላይ እንግልት እንደሚደርስ ገልፀዋል።

ኤንቢሲ ኒውስ ትናንት ማክሰኞ ባወጣው ዘገባ ቁጥራቸው ወደ ሰላሳ የሚጠጉ ፍልሰተኛ ልጆች የተናገሩት የያዙ የጤና እና ሰብዓዊ አገልግሎት ሚኒስቴር ሥራ ኃላፊዎች ዶሴዎች ማግኘቱን ገልጿል።

ልጆቹ ንፅህ የውስጥ ልብስ እንዲሰጠን የመሳሰለ ጥያቄ ብንጠይቅ ጠባቂዎቹ ይናደዳሉ ብለን እንፈራለን የሚል እና ሌሎችም ብሶቶች ማሰማታቸውንም ዘገባው አውስቷል።

በአሪዞናው የፍልሰተኛ ማቆያ ማዕከል ያለ አንድ ልጅ ስለምግቡ እና የመጠጥ ውሃ ጣዕም ስናማርር የድንበር ጥበቃ አባላቱ ተናደው የምንተኛበትን ምንጣፍ ነጥቀውን ሲሚንቶ ወለል ላይ አስተኝተውናል ማለቱን ኤንቢሲ ጠቅሷል።

በሥራ ኃላፊዎች ዶሴዎች ላይ የታዩት ልጆቹ በሙሉ ህጉ ከሚፈቅደው ጊዜ በላይ በማቆያ ማዕከሉ የተያዙ እንደሆኑ ነው ዘገባው ያመለከተው።

የድንበር ጥበቃ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ በበኩላቸው በሪፖርቱ የቀረቡት ውንጀላዎች ከተለመደው የመስሪያ ቤታችን አሰራር የሚጣጣም አይደለም፣ ምርመራ እናካሂዳለን ማለቱን ሪፖርቱ ጠቅሷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG