በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤልና የሁለቱ አረብ ሃገራት “የአብርሃም ሥምምነት”


የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እና ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እና ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት ማክሰኞ በዋይት ኃውስ የተከናወነውን “የአብርሃም ሥምምነት” አስተናግደዋል፡፡ ሥምምነቱ እስራኤል ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ባህሬን ጋር ይፋዊና መደበኛ ግንኙነት መመስረቱን የሚያበስር ነው፡፡ ባለሙያዎች እንደሚሉት ለእስራኤል ዲፕሎማሲያዊ ዕውቅና በመስጠት የተፈጸመው ሥምምነት በአካባቢው ለአሥርት ዓመታት የቆየውን ስትራቴጂ ለውጥ የሚያመልከት ነው፡፡ እስራኤልም በአጸፋው የሁለት መንግሥታት ሥምምነቶችን በማክበር ለፍልስጤም ነጻነት ለማረጋገጥ መሥራት ይኖርባታል፡፡

ፕሬዚዳንት ትረምፕ “የአዲሱ የመካከለኛ ምሥራቅ መወለድ ነው” ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህን የተናገሩት የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች እና ባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በዋይት ኃውስ ተገኝተው ሥምምነቱን በተፈራረሙበት ወቅት ነው፡፡ “የአብርሃም ሥምምነት” ተብሎ የሚጠራው ይህ ሥምምነት ሁለቱን የባህረ ሰላጤው አረብ ሃገራት ከእስራኤል ጋር በወዳጅነት የሚያስተሳሰር መሆኑ ተነግሯል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

እስራኤልና የሁለቱ አረብ ሃገራት “የአብርሃም ሥምምነት”
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:22 0:00


XS
SM
MD
LG