በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስና የሜክስኮ ባለሥልጣናት በፍልስተኞች ጉዳይ ይወያያሉ


ፍልሰተኞች ታፓቹላ፣ ሜክሲኮ፣ እአአ 24/2023
ፍልሰተኞች ታፓቹላ፣ ሜክሲኮ፣ እአአ 24/2023

የዩናይትድ ስቴትስ እና የሜክሲኮ ባለሥልጣናት ዋይት ሐው ከቅርብ ወራት ወዲህ በአካባቢው በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል ሲል በገለጸው የፍልስተኞች ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ዛሬ ረቡዕ ሜክሲኮ ሲቲ ውስጥ ይገናኛሉ፡፡

በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር አሌሃንድሮ ማዮርካስ እና የዋይት ሀውስ የሀገር ውስጥ ደህንነት አማካሪ ሊዝ ሸርዉድ-ራንዳል የዩናይትድ ስቴትስን በመወከል ይገኛሉ፡፡

ውይይቱ ከሜክሲኮ በኩል የሜክሲኮን የፀጥታ ካቢኔን ጨምሮ ስብሰባውን ከሚያስተናግዱት ከሜክሲኮ ፕሬዝዳንት አንድሬስ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶርን ጋር እንደሚካሄድ ተመልክቷል፡፡

የሜክሲኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ የዛሬ ረቡዕ ስብሰባ፣ ለፍልስተኞ ህጋዊ መንገዶችን ማስፋትን ጨምሮ፣ በፍልስት ጉዳዮች ላይ ያለውን ትብብር ዳግመኛ ለማረጋገጥ እድል ይሰጣል ብሏል፡፡

ዛሬ ከሚደረገው ስብሰባ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ፣ ወደ 6,000 የሚጠጉ የስደተኞች ቡድን በሜክሲኮ ደቡብ ጓቲማላ ድንበር አቅራቢያ ከምትገኘው ታፓቹላ ተነስተው የአሜሪካን ድንበር አቁርጠው ለመግባት መሞከራቸው ተመልክቷል፡፡

ይህ የፍልስተኞች ቁጥር ከአንድ አመት ወዲህ ከታዩት ትልቅ የፍልስተኞች ቡድኖች ውስጥ እንደሚካተት ተነግሯል፡፡

ሜክሲኮ እንደ ቬንዙዌላ፣ ኒካራጓ እና ኩባ ካሉ ሀገራት የጥገኝነት ወይም ለሌላ የስደት ዓይነት የሚያበቁ ህጎችን ባለመከተል ተቀባይነት አጥተው ከአሜሪካ ድንበር የተመለሱ ፍልስተኞችን ለመቀበል ባላፈው ግንቦት ወር ተስማምታለች።

የዩናይትድ ስቴትስ የጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ በህዳር ወር 242,418 ፍልስተኞች መዝግቧል፡፡ ይህ በህዳርና ባላፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ከነበረው ጋር ተቀራራቢ ቁጥር ነው ተብሏል፡፡ እኤአ በህዳር 2022 ግን የ70ሺ ብልጫ ማሳየቱም ተጠቅሷል፡፡

የሚኪሲኮ ፕሬዚዳንት ሎፔዝ ኦባርዶር ባላፈው ዓርብ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ እና ሜክስኮ በጋራ አብረው መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

ሰዎች ቤታቸውን ትተው የሚሰደዱባቸውን መሠረታዊችን ችግር ከመፍታት ጋር ፍልሰት ስርዓት ባለው መንገድ እንዲካሄድ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ አጽንኦት ሰጥተውታል፡፡

ዓርብ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሎፔዝ ኦብራዶር ሜክሲኮ እና ዩናይትድ ስቴትስ በጋራ መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ በመግለጽ ስደትን በሥርዓት እንዲቀጥል እና ሰዎች ቤታቸውን እንዲለቁ የሚያደርጓቸውን ምክንያቶች ለመፍታት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

ፍልስት በምርጫ ሳይሆን የግዴታ ጉዳይ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG