በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሜሪላንድ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ላይ ከወደቀው አውሮፕላን 2 ሰዎች ተረፉ


በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ላይ የወቀው አውሮፕላን
በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ላይ የወቀው አውሮፕላን

ዩናይትድ ስቴትስ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት ሞንትጎምሪ ውስጥ ትናንት እሁድ ማምሻው ላይ ሁለት ሰዎችን ይዞ ይጓዝ የነበረ አንድ ትንሽ አውሮፕላን በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ላይ በመወደቁ በአካባቢው ከፍተኛ የመብራት መቆራረጥ መድረሱ ተነገረ፡፡

አውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ሌሊቱን ጭምር በተደረገ ጥረት ማውጣት የተቻለ ሲሆን ሁለቱም ሰዎች ከአውሮፕላኑ ወደ ምድር እንዲወርዱ መደረጋቸው ተነግሯል፡፡

የፌዴራል አቬይሽን ባለሥልጣን እንዳስታወቀው ከኒው ዮርክ ዋይት ፕሌይን የተነሳው አውሮፕላን ሞንትጎምሪ ጌትስበርግ ሲደርስ ከመሬት 30 ሜትር ከፍታ ካለው የኤልክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ላይ የወደቀው እሁድ ማምሻው ላይ ለአስራት ሁለት 20 ጉዳይ እንደነበር ተመልክቷል፡፡

የሞንትጎመሪ የእሳትና አደጋ መከላከል ቃል ቀባይ በትዊት ገጻቸው ላይ ሁለቱ ሰዎች ከዋሽንግተን የ65 ዓመቱ ፓይለት ፓትሪክ መርክል እና የ66 ዓመቱ መንገደኛ ጃን ዊሊያምስ ከሉዊዚያና መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG