በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካሊፍርኒያው ጥቃት ለተገደሉት 6 ሰዎች ሻማ ማብራት ስነ ሥርዓት ተካሄደ


በካሊፎርኒያ ግዛት ሳክራሜንቶ ውስጥ በተካሄድ የጅምላ ጥቃት የተገደሉትን ስድስት ሰዎች የሚዘክር የሻማ ማብራት ሥነ ስርዓት ትናንት ምሽቱን ተካሂዷል፡፡ 
በካሊፎርኒያ ግዛት ሳክራሜንቶ ውስጥ በተካሄድ የጅምላ ጥቃት የተገደሉትን ስድስት ሰዎች የሚዘክር የሻማ ማብራት ሥነ ስርዓት ትናንት ምሽቱን ተካሂዷል፡፡ 

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ባለፈው እሁድ በካሊፎርኒያ ግዛት ሳክራሜንቶ ውስጥ በተካሄድ የጅምላ ጥቃት የተገደሉትን ስድስት ሰዎች የሚዘክር የሻማ ማብራት ሥነ ስርዓት ትናንት ምሽቱን ተካሂዷል፡፡

በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡት እድሜያቸው ከ21 እስከ 57 የሚደርስ ሦስት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ናቸው፡፡ ሌሎች 12 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል፡፡

ሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሳክራሜንቶ ከንቲባ ዳሬል ስቲንበርግ እንዲህ ብለዋል፤

ዛሬ በዚህ ስፍራ የተገኘነው ለዮናታን ነው፤ ለመሊንዳ ለሰርጊዮ ለዳቬዝና ለያሚል ነው፡፡ ዛሬ እዚህ ትርጉም አልባ አሟሟታቸውን ለመዘከር ከሚወዷቸውና ዛሬ በመካከላችን ከሚገኙት አንዳንዶቹ ቤተሰቦቻቸ ጋር ተሰብሰበናል፡፡

ከንቲባው በስፍራው ለተገኙት ሀዘንተኞች ሲናገሩ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ የሚደርሰው ጥቃት (ጋን ቫይለንስ) ያለምንም ልዩነት ሁሉንም ሰዎች እየገደለና እያቆሰለ ያለ ህመም ነው ብለዋል፡፡

እሁድ ከሌሊቱ 8 ሰዓት ላይ መጠጥ ቤቶች እንደተዘጉ በክፍለ ግዛቱ ምክር ቤት አቅራቢያ ለተሰነዘረው ጥቃት ተጠርጣሪ የሆነው የ26 ዓመት ወጣት ዳንድሬ ማርትን ዛሬ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG