በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ በየቀኑ ከሚጠጡት፣ በየቀኑ ማሪዋና የሚጠቀሙት በልጠው ተገኙ


የማሪዋና ተክሎች ሳን ፍራንሲስኮ ከሚገኝ ሱቅ እአአ መጋቢት 20/2023
የማሪዋና ተክሎች ሳን ፍራንሲስኮ ከሚገኝ ሱቅ እአአ መጋቢት 20/2023

በአሜሪካ በየቀኑ በሚባል ደረጃ ማሪዋና የሚጠቀሙት ሰዎች ቁጥር፣ በየቀኑ አልኮል ከሚጠጡት ሰዎች ቁጥር በልጦ መታየቱን አንድ አዲስ ጥናት አመለከተ።

ዛሬ ረቡዕ “አዲክሽን” በተባለውና በአሜሪካ የትንባሆ፣ አልኮል እና አደንዛዥ እጽን በተመለከተ በሚያደርገው ጥናት ተአማኒነት ባተረፈው መጽሔት የወጣው ጥናት እንዳመለከተው፣ በእ.አ.አ 2022 ዓ.ም የማሪዋና ተጠቃሚዎች ቁጥር ከጠጪዎች ቁጥር ለመጀመሪያ ጊዜ በልጦ ተገኝቷል። በዓመቱ 17.7 ሚሊዮን ሰዎች በየቀኑ ማሪዋና ሲጠቀሙ፣ 14.7 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ በየቀኑ እነደሚጠጡ ጥናቱ ጠቁሟል። በተደጋጋሚ ማሪዋና የሚጠቀሙቱ ለሱስ እንደሚዳረጉ እና ከማሪዋና ጋራ ተያይዞ ለሚመጣው”ሳይኮስስ” ወይም ከእውነታ ጋራ መጣጣም አለመቻልን ሊያስከተል እንደሚችልም ጥናቱ አመልክቷል።

40 በመቶ የማሪዋና ተጠቃሚዎች በየቀኑ እንደሚወስዱም ተመልክቷል።

በየግዛቱ ማሪዋና ለህክምና ወይም ለመዝናናት በሕግ መፈቀዱ ለለውጡ ምክንያት እንደሆነም ተመልክቷል።

በፌዴራል ሕግ ማሪዋና መጠቀም አሁንም ክልክል ነው። ሆኖም ግን ከተመደበበት አደገኛ እጽ ደረጃ ዝቅ እንደሚያደርግ ፌዴራል መንግሥቱ ፍንጭ ሰጥቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG