በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስትን በድጋሚ ሆስፒታል ገቡ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን እአአ የካቲት 1/2024.
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን እአአ የካቲት 1/2024.

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን ትናንት እሁድ እንደገና ሆስፒታል ገብተዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሩ (ፔንታገን) እንዳስታወቀው በፕሮስቴት እጢ ካንሰር እያገገሙ የነበሩት ሚኒስትሩ ሥልጣናቸውን ለምክትላቸው አስተላልፈዋል፡፡

አጣዳፊ የፊኛ ህመም ምልክት የታየባቸው ኦስትን የህክምና ክትትል እንዲያገኙ በደህንነት ጠባቂዎቻቸው ወደ ዋልተር ሪድ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የፔንታገን ቃል አቀባይ ሜጀር ጀኔራል ፓት ራይደር በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

ኦስትን መጀመሪያ ላይ ሥራቸውናን ኃላፊነታቸውን ለመቀጠል አስበው የነበረ ቢሆንም እያደር ግን እነዚያን ኃላፊነቶቻቸውን ለምክትል የመከላከያ ሚኒስትሩ ካትሊን ሂክስ ማስተላለፋቸውን ራይደር አክለው ገልጸዋል፡፡

ስለ መከላከያ ሚኒስትሩ ሆስፒታል መግባት የጠቅላይ ኤታማ ማዦር ሹሙ ፣ ዋይት ሀውስ እና ምክር ቤቱ እንዲያውቀው መደረጉ ተገልጿል፡፡

ኦስትን ባላፈው ታህሳስ የፕሮስቴት እጢ ካንሰር ምርመራና የቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎላቸዋል፡፡ የአውሮፓውያኑን አዲስ ዓመት ለሁለት ሳምንት በቆዩበት በዚሁ የዋልተሪድ ሆስፒታል ውስጥ ማሳለፋቸው ተጠቅሷል፡፡

ባላፈው ታህሳስ ውስጥ ስለሆስፒታል ቆይታቸውም ሆነ ስለ ካንሰር ምርምራና ህክምና የተደረገላቸው ስለመሆኑ ለፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ለምክር ቤቱም ሆነ ለምክትል የመከላከያ ሚኒስትሩ አለማሳወቃቸው ተገልጿል፡፡

የሁኔታው በሚስጥር መያዝ የጠቅላላ ኦዲተሩ እና የፔንታገን የውስጥ ምርመራ እንዲካሄድ ምክንያት ሆኗል፡፡

ሚኒስትሩ የሳቸው ሆስፒታል መግባት በሚስጥር እንዲያዝ ለሠራተኞቻቸው ምንም ዓይነት መመሪያ አለመስጠታቸውን ቀደም ሲል ገልጸው ነበር፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG