በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶሪያዊው በሊባኖስ የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ተኮሰ

የሊባኖስ ደህንነት ሰራተኞች አሜሪካ ኤምባሲ በሚወስደው መንገድ በጥበቃ ላይ ቤይሩት ሰሜናዊ ዳርቻ፣ ሊባኖስ፣ እአአ ሰኔ 5/2024
የሊባኖስ ደህንነት ሰራተኞች አሜሪካ ኤምባሲ በሚወስደው መንገድ በጥበቃ ላይ ቤይሩት ሰሜናዊ ዳርቻ፣ ሊባኖስ፣ እአአ ሰኔ 5/2024

ዜግነቱ ሶሪያዊ የሆነ አንድ ግለሰብ በሊባኖስ የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ዛሬ ረቡዕ ተኩስ ከፍቶ እንደነበር ታውቋል።

በሠራተኞቹ ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ኤምባሲው አስታውቋል።

ግለሰቡ በኤምባሲው ላይ ተኩስ መክፈቱን ተከትሎ፣ ከወታደሮች ጋራ የተኩስ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን፣ ተጎድቶ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን የሃገሪቱ ሠራዊት አስታውቋል።

በጉዳዩ ላይ ምርመራ በመካሄድ ላይ መሆኑና ከፀጥታ ባለሥልጣናት ጋራ በቅርብ በመሥራት ላይ መሆኑን ኤምባሲው በማኅበራዊ ሚዲያ አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG