በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ ጉዳይ ውይይት ተካሄደ


ማይክ ፖምፒዮ
ማይክ ፖምፒዮ

በሳዑዲ አረቢያዊ ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ መገደል አሁንም ድረስ ንዴቱ ያልበረደላቸው አብዛኞቹ የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት፣ ዛሬ በዝግ ስብሰባ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ እና ከመከላከያ ሚኒስትሩ ጂም ማቲስ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

በሳዑዲ አረቢያዊ ጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ መገደል አሁንም ድረስ ንዴቱ ያልበረደላቸው አብዛኞቹ የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት፣ ዛሬ በዝግ ስብሰባ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ እና ከመከላከያ ሚኒስትሩ ጂም ማቲስ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ የኻሾግዢ ገዳዮች ማንነት ታውቆ፣ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጥረት እያደረገች ቢሆንም፣ ሳዑዲ አረቢያ በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር የምትጫወተው መሠረታዊ ቸል ሊባል አይገባም ሲሉ መከላከያ ሚኒስትሩ ጂም ማቲስ አስረድተዋል።

ከሳዑዲ ተሰዶ በዩናይትድ ስቴትስ ይኖር የነበረው ኻሾግዢ ባለፈው ወር የተገደለው፣ በሳዑዲ የቱርክ ቆንሲላ ጽሕፈት ቤት ውስጥ መሆኑ ይታወሳል።

በዚህ ሚሥጥራዊ ስብሰባ ላይ የሲአይኤ ዳይሬክተር ጂና ሐስፔል ባለመወከላቸው በሁለቱም ፓርቲዎች ሕግ አርቃቂዎች ተወግዘዋል።

በስብሰባው ላይ የደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ተወካይ ተገኝቶ ፕሬዚዳንት ትረምፕ ከሳዑዲው አልጋወራሽ ሞሃመድ ቢን ሣልማን የሰሙትን ለምክር ቤቱ እንዲይስረዱ እፈልጋለሁ ሲሉ የደቡብ ካሮላይናው ሪፖብሊካን ሴናተር ሊንድሲ ግራም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

የዴላዌሩ ዲሞክራት ሴናተር ክሪስ ኩንስ በበኩላቸው የሲአይኤ ዳይሬክተር ጂና ሐስፔል ማብራሪያ የማይሰጡን - ምናልባት ሁለቱ አስቀድመው ከድምዳሜ የደረሱበትን ጉዳይ እንዳይነግሩን ሊሆን ይችላል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

እስካሁን በተከታታይ የወጡ ዘገባዎች፣ የሳዑዲው አልጋወራሽ ሣልማን፣ የኻሾግዢን ግድያ ሳያዝዙ እንዳልቀረ ሲአይኤ ገምግሟል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG