ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤት አባላት በመንግሥት ባጀትና በኢሚግረሽን ጉዳይ ሥምምነት ላይ ለመድረስ ጊዜ እያጠረባቸው ነው።
በባጀት ምደባ ላይ ያለው ትግል በመጪው ሳምንት የመንግሥት ሥራ መዘጋትን ሊያስከትል ይችላል። ዲሞክራት የምክር ቤት አባላት ከ8መቶ ሺህ በላይ የሚሆኑት ወጣት ፈላሾች ጉዳይ ከማንኛውም ዓይነት የባጀት ሥምምነት ጋር እንዲያዝ ይፈልጋሉ።
በልጅነታቸው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለገቡት ሕጋዊ ፈቃድ ለሌላቸው ፍልሰተኞች የተሰጠው የመኖርያ ፈቃድ እንዲቀጥል ነው ዲሞክራቶቹ የሚፈልጉት።
አንድ የሕግ መምርያ አባላት የሆኑ ሪፖብሊካውያን ቡድን ሰፋ ያለ ይዘት ያለው የኢሚግረሽን ለውጥ እንዲደረግ የሚጠይቅ ሃሳብ አቅርቧል። ዲሞክራቶቹ ያቀረቡት ማሻሻያ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በልጅንታቸው እዚህ አገር ሲገቡ የተሰጣቸው ጊዚያዊ ፈቃድ ሲያበቃ ለሦስት ዓመታት እንዲራዘም የሚለውን ያጠቃልላል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ