በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ የኬንያን ፕሬዚዳንት በኃይት ሃውስ ተቀብለው አነጋገሯቸው

ሀገራቸው ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የጋርዮሽ ንግድን ለማሳደግና የአሜሪካውያንን መዋዕለ ንዋይ መዳቢዎች ለመሳብ እንደምትፈልግ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አስታውቀዋል።

ሀገራቸው ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የጋርዮሽ ንግድን ለማሳደግና የአሜሪካውያንን መዋዕለ ንዋይ መዳቢዎች ለመሳብ እንደምትፈልግ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አስታውቀዋል።

ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትላንት የኬንያውን መሪ በኃይት ሃውስ ቤተ መንግሥት ተቀብለው በንግድና የፀጥታ ጥበቃ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ውይይቶች አካሂደዋል።

ሁለቱ መሪዎች ትላንት ተገናኝተው ከመነጋገራቸው አስቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሀገራቸው ሙስናን በመዋጋትና ለባዕዳን መዋዕለ ንዋይ መዳቢዎች የሚያስፈልገውን የፀጥታ ጥበቃ በማጠናከር ላይ መሆኗን አስረድተዋል።

የኬንያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ፣ በደቡብ ሱዳንና በሱማልያ መረጋጋት እንዲፈጠር ጥረቶች መደረጋቸውንም አስረድተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ትረምፕ የኬንያን ፕሬዚዳንት በኃይት ሃውስ ተቀብለው አነጋገሯቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:58 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG