በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ የተቃዋሚዎችን መብት እንድታከብር አሜሪካ ጠየቀች


ፖሊስ ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞችን በአስለቃሽ ጭስ ሲበትን ናይሮቢ፤ ኬንያ
ፖሊስ ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞችን በአስለቃሽ ጭስ ሲበትን ናይሮቢ፤ ኬንያ

በኬንያ የታክስ ጭማሪን በመቃወም በተደረጉ ሰልፎች ላይ ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ፣ መንግስት ሰላማዊ የሆነ ተቃውሞ የማድረግን መብት እንዲያከብር አሜሪካ ዛሬ ረቡዕ ጥሪ አድርጋለች፡፡

“ሠላማዊ ሕዝባዊ ስብሰባ የማድረግ መብታቸውን በመጠቀም ላይ ያሉ ኬንውያን አደጋ ላይ እንዳይወድቁ ጥንቃቄ እንዲደረግ መወትወታችንን እንቀጥላልን” ሲሉ የአሜሪካው ብሔራዊ የደህንነት ም/ ቤት ቃል አቀባ ጃን ከርቢ ለዜና ሰዎች ተናግረዋል።

“መብቱ በኬንያ ሕገ መንግስት የተጠበቀ በመሆኑ፣ መከበር አለብት የሚል እምነት አለን” ሲሉ ከርቢ አክለዋል።

በትላንትናው ዕለት ተቃዋሚዎች ፓርላማውን መውረራቸውና እና በርካቶች በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን ተከትሎ፣ የሃገሪቱ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ የታክስ ማሻሻያ ሕጉን በፊርማቸው እንደማያጸድቁ ዛሬ ረቡዕ አስታውቀዋል።

የታክስ ጭማሪው ያስፈለገው የውጪ ዕዳን ለመክፈል እንደሆነ መንግስት ሲገልጽ ቆይቷል። ኬንያውያን በበኩላቸው የታክስ ጭማሪው ባለው የኑሮ ጫና ላይ ይበልጥ ስቃይ ውስጥ እንደሚከታቸው ይገልጻሉ። ትላንት በፓርላማው የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ መንግስት መከላከያ ሠራዊቱን አሰማርቷል።

ሁኔታውን “የሃገር ክህደት” ሲሉ የገለጹት ሩቶ፣ የታክስ ሕጉ “ሰፊ ቅሬታ” እንዳስከትለና እና ሕዝቡ ላሰማው ድምጽ ምላሽ እንደስጡ አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG