በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ "ተሰልዬ ከነበረ ይጣራልኝ" አሉ

የዩናየትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዛሬ ሁለት ዓመት በተካሄደው የዩናየትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት የፖለቲካ ተነሣሽነት የታጀበ ስለላ በምረጡኝ ዘመቻ ቡድናቸው ላይ ተካሂዶ እንደሆነ እንዲጣራላቸው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ባሳደሩት ጫና የፍትሕ መሥሪያ ቤቱ ጠቅላይ መርማሪው ሁኔታውን እንዲያይ መጠየቁን አስታወቀ።

የዛሬ ሁለት ዓመት በተካሄደው የዩናየትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት የፖለቲካ ተነሣሽነት የታጀበ ስለላ በምረጡኝ ዘመቻ ቡድናቸው ላይ ተካሂዶ እንደሆነ እንዲጣራላቸው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ባሳደሩት ጫና የፍትሕ መሥሪያ ቤቱ ጠቅላይ መርማሪው ሁኔታውን እንዲያይ መጠየቁን አስታወቀ።

ለመሥሪያ ቤቱ እርምጃውን የወሰደው ፕሬዚዳንት ትረምፕ ትናንት ባስገቡት ደብዳቤ ፌደራሉ የምርመራ ቢሮ - ኤፍቢአይ በዘመቻቸው ውስጥ ሠርጎ ገብቶ እንደነበረ ወይም አለመግባቱን፤ ገብቶ ከነበረም የፖለቲካ ምክንያት ይኑረው አይኑረው፤ ምናልባትም በወቅቱ ከኦባማ አስተዳደር ከየትኛውም ባለሥልጣን ቢሆን የተሰጠ መመሪያ ይኑር አይኑር እንዲጣራላቸው ከጠየቁ በኋላ ነው።

ሩሲያ ባለፈው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት እጆቿን አስገብታ እንደሆነ እያጣሩ ያሉትን ልዩ መርማሪ ራበርት መለርን ሥራ በቅርብ የሚከታተሉት ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ሮድ ሮዜንስታይን በሰጡት ቃል “ማንም ቢሆን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ዘመቻ ቡድን አባላትን አግባብ ለሌለው ምክንያት ሰልሎ ከሆነ ልናውቅና ተገቢውን እርምጃ ልንወስድ ይገባናል” ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG